Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 4:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 አባቶቻችሁን ወድዶአልና ከእነርሱ በኋላ ዘራቸውን መረጠ፥ ከእናንተ ጋር ሆኖ በታላቅ ኃይሉ ከግብጽ አወጣችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 አባቶችህን ከመውደዱ የተነሣና ከእነርሱም በኋላ ዘራቸውን ስለ መረጠ፣ ከአንተ ጋራ በመሆን በታላቅ ኀይሉ ከግብጽ አወጣህ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 የቀድሞ አባቶቻችሁን በመውደዱ እናንተን ልጆቻቸውን ስለ መረጣችሁ በታላቅ ኀይሉ እርሱ ራሱ ከግብጽ አወጣችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 አባ​ቶ​ች​ህን ወድ​ዶ​አ​ልና ከእ​ነ​ርሱ በኋላ ዘራ​ቸ​ውን መረጠ፤ ከአ​ን​ተም ጋር ሆኖ በታ​ላቅ ኀይሉ ከግ​ብፅ አወ​ጣህ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37-38 አባቶችህን ወድዶአልና ከእነርሱ በኋላ ዘራቸውን መረጠ፥ ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ከአንተ የጸኑትን ታላላቆችን አሕዛብ በፊትህ እንዲያወጣ፥ አንተንም እንዲያገባህ፥ ምድራቸውንም ርስት አድርጎ እንዲሰጥህ፥ ከአንተ ጋር ሆኖ በታላቅ ኃይሉ ከግብፅ አወጣህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 4:37
32 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ብቻ ጌታ ስለ አባቶችህ ደስ ብሎታል፥ እነርሱንም ወድዶአል፥ ከእነርሱም በኋላ እናንተን ዘራቸውን እንደ ዛሬው ሁሉ ከአሕዛብ ሁሉ መካከል መረጠ።


በጭንቃቸው ሁሉ እርሱ ተጨነቀ፥ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤ በፍቅሩና በርኅራኄውም ተቤዣቸው፥ በቀደመውም ዘመን ሁሉ አንሥቶ ተሸከማቸው።


እርሱም “እኔ ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፥ ዕረፍትም እሰጥሃለሁ” አለው።


እንዲህም ይሆናል በሚመጣው ጊዜ ልጅህ፦ ይህ ምንድነው? ብሎ በጠየቀህ ጊዜ እንዲህ ትለዋለህ፦ ጌታ በብርቱ እጅ ከባርነት ቤት ከግብጽ አወጣን፤


በእጅህ እንደ ምልክት በዐይኖችህም መካከል እንደ መታሰቢያ ይሁንልህ፥ የጌታ ሕግ በአፍህ እንዲሆን፥ ጌታ በብርቱ እጅ ከግብጽ አውጥቶሃልና።


ሙሴም ሕዝቡን አለ፦ ከባርነት ቤት ከግብጽ የወጣችሁበትን ይህንን ቀን አስቡ፥ ጌታ ከዚህ ቦታ በብርቱ እጅ አውጥቶአችኋልና ስለዚህ የቦካ እንጀራ አትብሉ።


አባቶችም የእነርሱ ናቸው፤ ከእነርሱም ዘር ክርስቶስ በሥጋ መጣ፤ እርሱም ከሁሉ በላይ የሆነ ለዘለዓለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን።


ወድጃችኋለሁ ይላል ጌታ፤ እናንተ ግን፦ “እንዴት ወደድከን?” ትላላችሁ። ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ይላል ጌታ። ሆኖም ያዕቆብን ወደድኩት።


በዚያን ዘመን፥ ይላል ጌታ፥ ለእስራኤል ወገኖች ሁሉ አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።


ከክፉ ነገር ሽሽ መልካምንም አድርግ፥ ሰላምን እሻ ተከተላትም።


አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፥ ዐይኖቼን በአንተ ላይ አጠናለሁ።


ጌታ ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ለማጽናት ዐይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። እንግዲህ አሁን የሞኞችን ተግባር ፈጽመሃል። ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ጦርነት ይደረግብሃል።”


ምድራቸውን እንድትወርስ የምትገባው ስለ ጽድቅህና ስለ ልብህ ቅንነት አይደለም፥ ነገር ግን ጌታ እግዚአብሔር ከፊትህ በሚያጠፋቸው በእነዚያ ሕዝቦች ኃጢአት ምክንያትና፥ ለአባቶችህ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅ፥ ለያዕቆብ፥ ጌታ የማለላቸውን ቃል እንዲፈጸም ነው።


ወይስ በፈተና፥ በተአምራት፥ በድንቅ፥ በጦርነት፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በሚያስፈራም ኃይል፥ በዐይናችሁ ፊት ጌታ አምላካችሁ እናንተን ከግብጽ ምድር እንዳወጣችሁ፥ አንድን ሕዝብ ከሌላ ሕዝብ መካከል ወስዶ የራሱ ሕዝብ ለማድረግ የሞከረ ሌላ አምላክ አለን?


ነገር ግን ጌታ እግዚአብሔር በለዓምን መስማት አልፈለገም፥ ጌታ እግዚአብሔር ወድዶሃልና እርግማኑን በረከት አደረገልህ።


በእርግጥ ሕዝቡን ይወዳል፤ ቅዱሳኑ ሁሉ በእጁ ናቸው፤ እነርሱም በእግሮችህ ሥር ይሰግዳሉ፤ መመሪያህንም ከአንተ ይቀበላሉ።


ስለ ብንያምም እንዲህ አለ፦ “በጌታ የተወደደ በእርሱ ዘንድ ተማምኖ ይኖራል፤ ቀኑን ሁሉ ይጠብቀዋል፤ በትከሻዎቹም መካከል ያርፋል።”


እጅህ አሕዛብን አባረረች፥ እነርሱንም ተከልህ፥ አሕዛብን አስጨንቀህ እነሱን አለመለምክ።


ጌታም ከሩቅ ተገለጠልኝ እንዲህም አለኝ፦ “በዘለዓለም ፍቅር ወድጄሻለሁ፤ ስለዚህ በጽኑ ፍቅር ሳብሁሽ።


እንዲህም ሆነ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ከተፈጸመ በኋላ በዚህ ቀን የጌታ ሠራዊት ሁሉ ከግብጽ ምድር ወጡ።


በዚያም ቀን ጌታ የእስራኤልን ልጆች ከሠራዊታቸው ጋር ከግብጽ ምድር አወጣ።


ወደ ጌታም በጮኽን ጊዜ ድምፃችንን ሰማ፥ መልአክንም ልኮ ከግብጽ አወጣን፤ እነሆም፥ በምድርህ ዳርቻ ባለችው ከተማ በቃዴስ ተቀምጠናል።


“ለጌታ አምላክህ አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና፥ በምድር ላይ ካሉት ሕዝቦች ሁሉ፥ ጌታ አምላክህ ለእርሱ የተለየህ ሕዝብ እንድትሆን መረጠህ።


በዓይኔ ፊት የከበርህና የተመሰገንህ ነህና፥ እኔም ወድጄሃለሁና ስለዚህ ሰዎችን ለአንተ፥ አሕዛብንም ለነፍስህ እሰጣለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች