Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 33:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ስለ ሌዊም እንዲህ አለ፦ “ማሳህ በተባለው ቦታ ለፈተንኸው፥ በመሪባ ውኃም ለተከራከርኸው፥ ቱሚምህን ለሌዊ ስጠው፥ ኡሪምህም ለዚህ ቅዱስ ሰው ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ስለ ሌዊም እንዲህ አለ፦ “ቱሚምህና ኡሪምህ፣ ለምታምነው ሰው ይሁን፤ ማሳህ በተባለው ቦታ ፈተንኸው፤ በመሪባም ውሃ ከርሱ ጋራ ተከራከርህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ስለ ሌዊም ነገድ እንዲህ አለ፦ “ጌታ ሆይ! በቱሚምና በዑሪም አማካይነት በማሳና በመሪባ ውሃ ዘንድ ተከራክረህ ለፈተንካቸው ለአገልጋዮችህ ለሌዋውያን ፈቃድህን ግለጥ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ስለ ሌዊም እን​ዲህ አለ፥ ለሌዊ ቃሉን፥ በመ​ከ​ራም ለፈ​ተ​ኑት፥ በክ​ር​ክር ውኃም ለሰ​ደ​ቡት፥ ለእ​ው​ነ​ተ​ኛው ሰው ጽድ​ቁን መልስ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ስለ ሌዊም እንዲህ አለ፥ 2 ቱሚምህና ኡሪምህ ለቅዱስህ ሰው ነው፥ 2 በማሳህ ለፈተንኸው፥ 2 በመሪባ ውኃም ለተከራከርኸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 33:8
25 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርሱም የዚያን ስፍራ ስም ማሳህና መሪባ ብሎ ጠራው፥ ይህም ስለ እስራኤል ልጆች ጥልና “ጌታ በመካከላችን ነው ወይስ አይደለም?” በማለት ጌታን ስለተፈታተኑት ነው።


በፍርዱ በደረት ኪስም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን ታደርጋለህ፥ በጌታ ፊት በገባ ጊዜ በአሮን ልብ ላይ ይሆናሉ፤ አሮንም በጌታ ፊት ሁልጊዜ የእስራኤልን ልጆች ፍርድ በልቡ ላይ ይሸከማል።


የእስራኤል ልጆች ከጌታ ጋር የተጣሉበት፥ እርሱም በመካከላቸው ቅዱስ መሆኑን የገለጠበት ይህ የመሪባ ውኃ ነው።


ሙሴንም፥ ጌታ የቀደሰውንም አሮንን በሰፈር ተመቀኙአቸው።


የደረት ኪስ በእርሱ ላይ አደረገ፤ በደረቱ ኪስም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን አኖረበት።


“በፊላደልፊያም ወዳለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፥ ‘ቅዱስና እውነተኛ የሆነው፥ የዳዊትም መክፈቻ ያለው፥ ሲከፍትም፥ ማንም የማይዘጋው፤ ሲዘጋም ማንም የማይከፍተው፤ እርሱ እንዲህ ይላል’፦


እንዲህ ያለው ቅዱስ፥ ነቀፋ የሌለበት፥ ንጹሕ፥ ከኃጢአተኞች የተለየ፥ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ ሊቀ ካህናት ሊኖረን ይገባል፤


ጫንቃውን ከሸክም፥ እጆቹንም በቅርጫት ከመገዛት አራቅሁ።


ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፥ ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም።


ገዢውም፦ በኡሪምና በቱሚም የሚፈርድ ካህን እስኪነሣ ደረስ ከተቀደሰው ነገር እንዳይበሉ ነገራቸው።


እኔም አልኋቸው፦ “እናንተ ለጌታ ተቀድሳችኋል፥ ዕቃዎቹም ቅዱስ ናቸው፤ ብሩና ወርቁም ለአባቶቻችን አምላክ ለጌታ በበጎ ፈቃድ የቀረበ መባ ነው፤


አስተዳዳሪውም፦ በኡሪምና በቱሚም የሚጠይቅ ካህን እስኪነሣ ድረስ ከቅዱሰ ቅዱሳን አትበሉም አላቸው።


ወደ ጌታ ቤት ግን ከካህናትና ከአገልጋዮቹ ሌዋውያን በቀር ማንም አይግባ፤ እነርሱ ቅዱሳን ናቸውና ይግቡ፤ ሕዝቡም ሁሉ ግን የጌታን ሕግ ይጠብቅ።


እርሱም ጌታን ጠየቀ፤ ጌታ ግን በሕልምም ሆነ በኡሪም ወይም በነቢያት አልመለሰለትም።


በመጨረሻም መልካም ነገር ሊያደርግልህ፥ ሊፈትንህ ሊያዋርድህም አባቶችህ ያላወቁትን መና በምድረ በዳ ያበላህን፥


በካህኑም በአልዓዛር ፊት ይቁም፤ እርሱም በጌታ ፊት በኡሪም ፍርድ ይጠይቅለት፤ እርሱ ከእርሱም ጋር የእስራኤል ልጆች ማኅበሩም ሁሉ በቃሉ ይውጡ፥ በቃሉም ይግቡ።”


ለቆሬም እርሱንም ለተከሉት ሁሉ እንዲህ ቡሎ ተናገረ፦ “ነገ ጠዋት ጌታ ለእርሱ የሆነውን ሰው፥ ቅዱስም ማን እንሆነ፥ ወደ እርሱም ለመቅረብ የተፈቀደለትን ሰው ያሳውቃል፤ የመረጠውንም ሰው ወደ እርሱ እንዲቀርብ ይፈቅድለታል።


ካህኑ ለአምላኩ የተቀደሰ ነውና አመንዝራይቱን ሴት ወይም የረከሰችውን አያግባ፤ ወይም በባልዋ የተፈታችውን አያግባ።


ከንጹህ ወርቅ ቅጠል ሥራ፥ በእርሱም ላይ እንደ ማኅተም ቅርጽ ‘ለጌታ የተቀደሰ’ የሚል ቅረጽበት።


“አሮን ወደ ወገኑ ይከማች፤ በመሪባ ውኃ ዘንድ በትእዛዜ ላይ ስላመፃችሁ ለእስራኤል ልጆች ወደ ሰጠኋት ምድር አይገባም።


“ ‘በማሳህ’ እንደ ፈተናችሁት ጌታ አምላካችሁን አትፈታተኑት።


የእውነት ትምህርት በአፉ ውስጥ ነበረ፥ በከንፈሩም ውስጥ ስሕተት አልተገኘም፤ ከእኔ ጋር በሰላምና በቅንነት ሄደ፥ ብዙዎችንም ከኃጢአት መለሰ።


ከእስራኤል ልጆች ርስት ለሌዋውያን የምትሰጡአቸውን ከተሞች እንዲሁ ስጡ፤ ከብዙዎቹ ብዙ፥ ከጥቂቶቹ ጥቂት ትወስዳላችሁ፤ እያንዳንዱ እንደ ወረሱት እንደ ርስታቸው መጠን ከከተሞቻቸው ለሌዋውያን ይሰጣሉ።”


“እንደገና በታቤራ፥ በማሳህም፥ በቂብሮት ሐታዋም ጌታን አስቆጣችሁት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች