ዘዳግም 32:50 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)50 ወንድምህ አሮን በሖር ተራራ ላይ እንደ ሞተና ወደ ወገኖቹ እንደ ተሰበሰበ ሁሉ፥ አንተም በወጣህበት በዚያ ተራራ ላይ ሙት፥ ወደ ወገኖችህም ተሰብሰብ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም50 ወንድምህ አሮን በሖር ተራራ ላይ እንደ ሞተና ወደ ወገኖቹ እንደ ተሰበሰበ ሁሉ፣ አንተም በወጣህበት በዚያ ተራራ ላይ ሙት፤ ወደ ወገኖችህም ተሰብሰብ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም50 ወንድምህ አሮን በሖር ተራራ ላይ ሞቶ ወደ ወገኖቹ እንደ ተቀላቀለ አንተም በዚሁ በነቦ ተራራ ላይ ሞተህ ከወገኖችህ ጋር ትቀላቀላለህ፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)50 ወንድምህ አሮን በሖር ተራራ እንደ ሞተ፥ ወደ ወገኖቹም እንደ ተጨመረ፥ በወጣህበት ተራራ ሙት፤ ወደ ወገኖችህም ተጨመር፤ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)50 ወንድምህም አሮን በሖር ተራራ እንደ ሞተ ወደ ወገኖቹም እንደ ተከማቸ፥ በወጣህበት ተራራ ሙት፥ ወደ ወገኖችህም ተከማች፤ ምዕራፉን ተመልከት |