Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 32:49 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

49 “ከኢያሪኮ ማዶ ባለው የሞዓብ ምድር፥ ከዓባሪም ተራራዎች አንዱ ወደ ሆነው ወደ ነቦ ተራራ ውጣ፥ ለእስራኤላውያን ርስት አድርጌ የምሰጣትን የከነዓንን ምድር አሻግረህ ተመልከት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

49 “ከኢያሪኮ ማዶ ባለው የሞዓብ ምድር፣ ከዓባሪም ተራሮች አንዱ ወደ ሆነው ወደ ናባው ተራራ ወጥተህ ለእስራኤላውያን ርስት አድርጌ የምሰጣትን የከነዓንን ምድር አሻግረህ ተመልከት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

49 “በሞአብ ምድር በኢያሪኮ ከተማ ፊት ለፊት ወደሚገኙት የዐባሪም ተራራዎች ሂድ፤ ወደ ነቦ ተራራም ውጣ፤ ከዚያም ለእስራኤል ሕዝብ የማወርሳትን የከነዓንን ምድር አሻግረህ ተመልከት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

49 “በኢ​ያ​ሪኮ አን​ጻር በሞ​ዓብ ምድር በዓ​ባ​ሪም ተራራ ውስጥ ወዳ​ለው ወደ ናባው ተራራ ውጣ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ርስት አድ​ርጌ የም​ሰ​ጣ​ቸ​ውን የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር እያት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

49 ወደዚህ በኢያሪኮ አንጻር በሞዓብ ምድር በዓባሪም ተራራ ውስጥ ወዳለው ወደ ናባው ተራራ ውጣ፥ ለእስራኤልም ልጆች ርስት አድርጌ የምሰጣቸውን የከነዓንን ምድር እይ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 32:49
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደዚህ ወደ ዓባሪም ተራራ ውጣ፥ ለእስራኤልም ልጆች የሰጠኋትን ምድር እይ፤


የምንኖርበት ምድራዊ ድንኳን የሆነው ሕይወት ቢፈርስ፥ በሰማይ ዘላለማዊ የሆነ በእጅ ያልተሠራ፥ በእግዚአብሔር የታነጸ መኖሪያ እንዳለን እናውቃለን።


ዐይኖችህ ንጉሡን በውበቱ ያዩታል፤ እነርሱም በሩቅ ያለች ምድርን ይመለከታሉ።


አባቶቻችንም ደግሞ በተራ ተቀብለው እግዚአብሔር በፊታቸው ያወጣቸውን የአሕዛብን አገር በያዙት ጊዜ ከኢያሱ ጋር አገቡአት፤ እስከ ዳዊት ዘመንም ድረስ ኖረች።


“እኔ ወደምሰጣችሁ ርስት ወደ ከነዓን ምድር በገባችሁ ጊዜ፥ በምትወርሱአት ምድር በአንድ ቤት ውስጥ የለምጽ ደዌ ባኖር፥


ይህን ዮርዳኖስን አትሻገርምና ወደ ፒስጋ ራስ ውጣ፥ ዓይንህንም አንሥተህ ወደ ምዕራብና ሰሜንም ወደ ደቡብም ወደ ምሥራቅም በዓይንህ ተመልከት።


“ውሽሞችሽ ሁሉ ጠፍተዋልና ወደ ሊባኖስ ወጥተሽ ጩኺ፤ በባሳን ላይ ድምፅሽን ከፍ አድርጊ፤ ከዓባሪምም ሆነሽ ጩኺ።


በእንግድነት የምትኖርባትን ምድር፥ የከነዓን ምድር ሁሉ፥ ለዘለዓለም ግዛት ይሆንህ ዘንድ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ፥ አምላክም እሆናቸዋለሁ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች