Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 32:41 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 የሚያንጸባርቅ ሰይፌን ከሳልኩ፥ እጄም ለፍርድ ካነሳችው፥ ጠላቶቼንም እበቀላለሁ፥ ለሚጠሉኝም ፍዳቸውን እመልሳለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 የሚያብረቀርቅ ሰይፌን ስዬ፣ እጄ ለፍርድ ስትይዘው፣ ባላጋራዎቼን እበቀላቸዋለሁ፤ የሚጠሉኝንም እንደ ሥራቸው እከፍላቸዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 የሚያንጸባርቅ ሰይፌን እስለዋለሁ፤ እኔም ፍርድን እፈርዳለሁ፤ ጠላቶቼንም እበቀላለሁ፤ ለሚጠሉኝም ዋጋቸውን እሰጣለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 ሰይ​ፌን እንደ መብ​ረቅ እስ​ላ​ታ​ለሁ፤ እጄም ፍር​ድን ትይ​ዛ​ለች፤ ለሚ​ጠ​ሉ​ኝም ፍዳ​ቸ​ውን እከ​ፍ​ላ​ለሁ፤ ጠላ​ቶ​ች​ንም እበ​ቀ​ላ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 የሚንቦገቦግ ሰይፌን እስለዋለሁ፥ 2 እጄም ፍርድን ትይዛለች፥ 2 ጠላቶቼንም እበቀላለሁ፥ 2 ለሚጠሉኝም ፍዳቸውን እከፍላለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 32:41
29 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታም በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ በእሳትና በሰይፉ ይፈርዳል፤ በጌታም ተወግተው የሞቱት ይበዛሉ።


በዚያም ቀን ጌታ ፈጣኑን እባብ ሌዋታንን፥ የሚጠቀለለውንም እባብ ሌዋታንን፥ በጠንካራ በታላቅ፥ በብርቱም ሰይፍ ይቀጣል፤ በባሕርም ውስጥ ያለውን ዘንዶ ይገድላል።


እግዚአብሔር ጻድቅ ዳኛ ነው፥ ሁልጊዜ ትክክለኛ ፈራጅ ነው፥


ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተወጠሩ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ፥


ስለ ሥጋ ማሰብ የእግዚአብሔር ጠላት መሆን ነው፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም አይችልም፥


ሐሜተኞች፥ አምላክን የሚጠሉ፥ የሚዳፈሩ፥ ትዕቢተኞች፥ ትምክህተኞች፥ ክፋትን የሚያውጠነጥኑ፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥


በነቢዩ በኢሳይያስ፥ እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፤ “እነሆ መንገድህን የሚያዘጋጅ መልእክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ፤


እናንተም ኢትዮጵያውያን ደግሞ፥ በሰይፌ ትገደላላችሁ።


ሰይፍ ወደ አሞን ልጆች ወደ ረባት፥ ወደ ይሁዳ፥ ወደ ተመሸገች ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመጣ መንገድን አድርግ።


ቀስትን የሚገትሩትን ቀስተኞችን ሁሉ በባቢሎን ላይ ጥሩአቸው፤ በዙሪያዋ ስፈሩባት አንድም ሰው አያምልጥ፤ በእስራኤል ቅዱስ በጌታ ላይ በኩራት አልታዘዝም ብላለችና እንደ ሥራዋ መጠን መልሱላት፥ እንዳደረገችም ሁሉ አድርጉባት።


የጩኸት ድምፅ ከከተማ፥ ድምፅም ከመቅደስ፥ በጠላቶቹ ላይ ፍዳን የሚያመጣ የጌታ ድምፅ ተሰምቶአል።


እንደ ሥራቸው መጠን እንዲሁ ቁጣን ለባላጋራዎቹ፥ ፍዳንም ለጠላቶቹ ይከፍላል፤ ለደሴቶችም ፍዳቸውን ይከፍላል።


ስለዚህ ጌታ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ የእስራኤል ኀያል እንዲህ ይላል፤ “በባላንጣዎቼ ላይ ቁጣዬን እገልጣለሁ፤ ጠላቶቼንም እበቀላለሁ።


በቀልና ብድራት መመለስ የእኔ ነው፤ እግራቸው የሚሰናከልበት ጊዜው፥ የመጥፊያቸው ቀን ቀርቧልና፥ የሚመጣባቸው ፍርድ ይፈጥናል።


በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፥ እኔ ጌታ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነኝና አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም።


አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም፤ እኔ ጌታ አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፥


ሙሴም ታቦቱ በተጓዘ ጊዜ ሁሉ እንዲህ ይል ነበር፦ “አቤቱ፥ ተነሣ፥ ጠላቶችህም ይበተኑ፥ የሚጠሉህም ከፊትህ ይሽሹ።”


እኔስ ከዓይንህ ፊት ተጣልሁ፥ በድንጋጤ አልሁ፥ አንተ ግን ወደ አንተ በጮኽሁ ጊዜ የልመናዬን ቃል ሰማኸኝ።


ስለዚህ እናንተ በግብጽ ምድር የምትኖሩ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ የጌታን ቃል ስሙ፤ በግብጽ ምድር ሁሉ በሚኖር በይሁዳ ሰው ሁሉ አፍ ስሜ ከእንግዲህ ወዲህ፦ ‘ሕያው በሆነ ጌታ እግዚአብሔር እምላለሁ!’ ተብሎ እንዳይጠራ፥ እነሆ፥ በታላቅ ስሜ ምያለሁ፥ ይላል ጌታ።


የአምላካችንን የጌታን በቀል ስለ መቅደሱም ሲል የሚበቀለውን በቀል በጽዮን ለመናገር ከባቢሎን ምድር የሚመጡትን የኰብላዮችና የስደተኞች ድምፅ አድምጡ።


ጌታ ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው፤ ጌታ ተበቃይና መዓት የተሞላ ነው፤ ጌታ ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፤ ቁጣን ለጠላቶቹ ያቆያል።


የሚጠሉትን በማጥፋት በፊታቸው ብድራት ይመልስባቸዋል፥ ለሚጠላው አይዘገይም፥ በፊቱ ብድራት ይመልስበታል።


ለማይመለስ ግን ሰይፉን ይስላል፥ ቀስቱን ወጥሮአል አዘጋጅቷልም፥


የተጻፈውን ፍርድ ያደርጉባቸው ዘንድ። ለቅዱሳን ሁሉ ይህች ክብር ናት። ሃሌ ሉያ።


ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ የአሦርን ንጉሥ እንደ ቀጣሁ እንዲሁ፥ እነሆ፥ የባቢሎንን ንጉሥና ምድሩን እቀጣለሁ።


በሕዝቤ በእስራኤል እጅ ኤዶምን እበቀላለሁ፤ እንደ ቁጣዬና እንደ መዓቴ መጠን በኤዶም ላይ ያደርጋሉ፤ በቀሌንም ያውቃሉ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ብዙም ሕዝቦች አንተን አይተው እንዲደነግጡ አደርጋለሁ፤ ሰይፌንም በፊታቸው ባወዛወዝሁ ጊዜ ነገሥታቶቻቸው ይንቀጠቀጣሉ፤ በወደቅህበትም ቀን እያንዳንዱ ስለ ነፍሱ በየጊዜው ሁሉ ይንቀጠቀጣሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች