Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 32:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ወጣት ወንዶችና ሴቶች፥ ሕፃኑንም ከሽማግሌ ጋር፥ በየመንገዱ ላይ በጦርነት፥ በቤትም ውስጥ በድንጋጤ ያጠፋቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ሰይፍ መንገድ ላይ ያስቀራቸዋል፤ ቤታቸውም ውስጥ ድንጋጤ ይነግሣል፤ ጕልማሳውና ልጃገረዷ፣ ሕፃኑና ሽማግሌው ይጠፋሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 በየመንገዱ ላይ ጦርነት ልጅ አልባ ያደርጋቸዋል፤ በቤት ውስጥ ፍርሀት ይሰፍናል፤ ወጣት ወንዶችና ሴቶች፥ ሕፃናትና ሽማግሌዎችም ያልቃሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ጐል​ማ​ሳ​ውን ከድ​ን​ግል፥ ሕፃ​ኑ​ንም ከሽ​ማ​ግሌ ጋር፥ በሜዳ ሰይፍ፥ በቤ​ትም ውስጥ ድን​ጋጤ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ጉልማሳውን ከድንግል፥ ሕፃኑንም ከሽማግሌ ጋር፥ 2 በሜዳ ሰይፍ፥ በቤትም ውስጥ ድንጋጤ ያጠፋቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 32:25
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚህም በኋላ ቀኑ ሊመሽ ሲል ወደ ሶርያውያን ሰፈር ሄዱ፤ ነገር ግን እዚያ ሲደርሱ ማንም ሰው አልነበረም፤


ስለዚህም የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ጉልማሶቻቸውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ገደላቸው፤ ጎልማሳውንና ድንግሊቱን ሽማግሌውንና አዛውንቱን አልማረም፤ ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው።


ነገር ግን፦ “በፈረስ ላይ ተቀምጠን እንሸሻለን እንጂ እንዲህ አይሆንም” አላችሁ፥ ስለዚህም ትሸሻላችሁ፤ ደግሞም፦ “በፈጣን ፈረስ ላይ እንቀመጣለን” አላችሁ፥ ስለዚህም የሚያሳድዷችሁ ፈጣኖች ይሆናሉ።


አሁንም የእስራኤል አምላክ የሠራዊት አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ከይሁዳ ወገን መካከል ትሩፍ እንዳይቀርላችሁ፥ ወንድንና ሴትን፥ ልጅንና ሕፃንን ከእናንተ ለማጥፋት ይህን ታላቅ ክፋት በራሳችሁ ላይ ለምን ታደርጋላችሁ?


እናንተም እንድትጠፉ በምድርም አሕዛብ ሁሉ መካከል መረገሚያና መሰደቢያ እንድትሆኑ፥ ለመቀመጥ በገባችሁባት በግብጽ ምድር ለሌሎች አማልክት አጥናችሁ በእጃችሁ ሥራ ለምን ታስቈጡኛላችሁ?


ሕፃናቱን ከመንገድ ጉልማሶቹንም ከአደባባይ ለማጥፋት ሞት ወደ መስኮታችን ደርሶአል ወደ ንጉሥ ቅጥሮቻችን ውስጥ ገብቶአል።


ሬስ። አቤቱ፥ ተጨንቄአለሁና፥ አንጀቴም ታውኮብኛልና ተመልከት፥ ዓመፃን ፈጽሞ አድርጌአለሁና ልቤ በውስጤ ተገላበጠብኝ፥ በሜዳ ሰይፍ ልጆቼን አጠፋ በቤትም ሞት አለ።


ዳሌጥ። ጡት የሚጠባው የሕፃን ምላስ ከጥም የተነሣ ወደ ትናጋው ተጣበቀ፥ ሕፃናት እንጀራ ለመኑ፥ የሚቈርስላቸውም የለም።


ሰይፍ በውጭ፥ ቸነፈርና ራብም ከቤት አለ፥ በሜዳ ያለው በሰይፍ ይሞታል፥ በከተማም ያለውን ቸነፈርና ራብ ይበላዋል።


ከመከሩትም ምክር የተነሣ ሰይፍ ከተሞቻቸውን ይመታል፥ ምዋርተኞቻቸውንም ይበላል ያጠፋልም።


ልጆቻቸውንም ቢያሳድጉ እንኳ አንድም ሰው ሳላስቀር ልጅ አልባ አደረጋቸዋለሁ፤ ከእነርሱም በራቅሁ ጊዜ ወዮላቸው!


ኤፍሬም ተመታ፥ ሥሩም ደረቀ፥ ፍሬም አያፈራም፤ ደግሞም ቢወልዱ እንኳ እጅግ የሚወዱአቸውን የማኅፀናቸውን ፍሬ እገድላለሁ።


የቃል ኪዳኑንም በቀል የሚበቀል ሰይፍ አመጣባችኋለሁ፤ ወደ ከተሞቻችሁም ትሰበሰባላችሁ፥ በመካከላችሁም ቸነፈርን እልክባችኋለሁ፤ በጠላትም እጅ ተላልፋችሁ ትሰጣላችሁ።


ትበላለህ፥ ነገር ግን አትጠግብም፥ ባዶነትህም በመካከልህ ይሆናል፤ ትወስዳለህ፥ ነገር ግን ወደ ደህንነት አታመጣም፥ ወደ ደህንነት ያመጣኸውንም ለሰይፍ እሰጣለሁ።


ወደ መቄዶንያም በመጣን ጊዜ፥ በሁሉ ነገር መከራን ተቀበልን እንጂ ሰውነታችን ዕረፍት አልነበረውም፤ ከውጭ ጠብ ነበረ፤ ከውስጥ ደግሞ ፍርሃት ነበረብን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች