Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 32:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 በሚያቃጥል ንዳድና በራብ ያልቃሉ፤ በወረርሽኝ መቅሠፍት ይጠፋሉ፤ ተናካሽ አውሬዎችን፥ ከሚሳቡ መርዘኛ እባቦችን ጋር እሰድባቸዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 የሚያጠፋ ራብ፣ በልቶ የሚጨርስ ቸነፈርና ከባድ መቅሠፍት እሰድድባቸዋለሁ፤ የአራዊትን ሹል ጥርስ፣ በምድር የሚሳብ የእባብ መርዝም እሰድድባቸዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 የሚጨርስ ራብ በእነርሱ ላይ እልካለሁ፤ በወረርሽኝና በመቅሠፍት ያልቃሉ፤ ተናካሽ አውሬዎችንና መርዘኛ ተናዳፊ እባቦችን እሰድባቸዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 በራብ ያል​ቃሉ፤ ለሰ​ማይ ወፎ​ችም መብል ይሆ​ናሉ፤ ኀይ​ላ​ቸ​ውም ይደ​ክ​ማል፥ ከም​ድር ይጠፉ ዘንድ የም​ድር አራ​ዊ​ትን ጥርስ፥ ከመ​ርዝ ጋር እል​ክ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 በራብ በንዳድ ይጠፋሉ፤ 2 በንዳድና በመራራ ጥፋት ያልቃሉ፤ 2 የአራዊትን ጥርስ፥ 2 የምድርንም እባብ መርዝ እሰድድባቸዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 32:24
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታ እግዚአብሔርም እባቡን አለው፦ “ይህን በማድረግህ፥ ከእንስሳት ከምድር አራዊትም ሁሉ ተለይተህ አንተ የተረገምህ ትሆናለህ፤ በሆድህም ትሄዳለህ፥ በሕይወትህም ዘመን ሁሉ አፈርን ትበላለህ።


ዕረፍትም መልካም መሆንዋን አየ፥ ምድሪቱም የለማች መሆንዋን፥ ትከሻውን ለመሸከም ዝቅ አደረገ፥ በከባድ ጉልበት ሥራ አገልጋይ ሆነ።


የእፉኝትን መርዝ ይጠባል፥ የእባብም ምላስ ይገድለዋል።


እንደ በረሃ እንጨት ፍም የኃያላን ፍላጾች የተሳሉ ናቸው።


በጨለማ ከሚጓዝ መቅሰፍት፥ በቀትር ከሚደመስስ አደጋ አትፈራም።


ተኩላና ጠቦት በአንድነት ይሠማራሉ፥ አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል፤ የእባብም መብል ትቢያ ይሆናል። በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ጉዳት አያደርሱም፥ አያጠፉምም፥ ይላል ጌታ።


ወደ ሜዳ ብወጣ፥ እነሆ፥ በሰይፍ የሞቱ አሉ፤ ወደ ከተማም ብገባ፥ እነሆ፥ በራብ ደዌ የከሱ አሉ፤ ነቢዩና ካህኑም ወደማያውቁት አገር ሄደዋልና።’”


ሰይፍን ለመግደል፥ ውሾችንም ለመጐተት፥ የሰማያትንም ወፎች የምድርንም አራዊት ለመብላትና ለማጥፋት፥ ዐራቱን ዓይነት ጥፋት ልኬባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ።


በክፉ በሽታ ይሞታሉ፤ አይለቀስላቸውም አይቀበሩምም፥ በመሬትም ላይ እንደ ጉድፍ ይሆናሉ፤ በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ፥ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።


እነሆ፥ መርዛቸውን አስማት የማያረክሰው እባቦችንና እፉኝቶችን በእናንተ መካከል እልካለሁ፤ እነርሱም ይነድፉአችኋል፥” ይላል ጌታ።


ከሚያቃጥል ከራብ ትኩሳት የተነሣ ቁርበታችን እንደ ምድጃ ጠቈረ።


ክፉ አውሬ በምድሪቱ እንዲያልፍ ባደርግ፥ ልጅ አልባ ቢያደርጋት፥ በአውሬው ምክንያት ማንም እንዳያልፍባት ባድማ ብትሆን፥


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኢየሩሳሌም ላይ አራቱን ክፉ ፍርዶቼን ሰይፍ፥ ራብ፥ ክፉ አውሬና ቸነፈር፥ ሰውንና እንስሳን ከእርሷ ለማጥፋት ብሰድድም፥


ራብንና ክፉዎችን አራዊት እሰድድባችኋለሁ፥ ልጆችሽን ያሳጡሻል፥ ቸነፈርና ደምም በአንቺ በኩል ያልፋሉ፥ ሰይፍንም አመጣብሻለሁ። እኔ ጌታ ይህን ተናግሬአለሁ።


በመካከላችሁም የዱር አራዊትን እለቅባችኋለሁ፤ ልጆቻችሁንም ይነጥቁአችኋል፥ እንሰሶቻችሁንም ያጠፉባችኋል፥ እናንተንም ቁጥራችሁን ያመነምኑታል፤ መንገዶቻችሁም የተራቈቱ ይሆናሉ።


በቀርሜሎስም ራስ ላይ ቢሸሸጉ እንኳ አድኜ ከዚያ አወጣቸዋለሁ፤ በጥልቅ ባሕርም ውስጥ ከዓይኔ ቢደበቁ እንኳ ከዚያ እባቡን አዝዛለሁ፥ እርሱም ይነድፋቸዋል፤


እንደ እባብ አፈር ይልሳሉ፥ በምድር እንደሚሳቡ ፍጥረታት እየተንቀጠቀጡ ከምሽጋቸው ይመጣሉ፤ በፍርሃት ወደ ጌታ አምላካችን ይመጣሉ፥ ከአንተ የተነሣ ይፈራሉ።


ቸነፈር በፊቱ ይሄዳል፥ መቅሠፍትም ከእግሩ ይወጣል።


ጌታ እስክትጠፋ ድረስ በሚቀሥፍ በሽታ ንዳድና ዕባጭ፥ ኀይለኛ ሙቀትና ድርቅ፥ ዋግና አረማሞ ይመታሃል።


ጌታ የሚያስነሣብህን ጠላቶችህን ታገለግላለህ፤ በራብና በጥማት፥ በእርዛትና በማጣት እስኪያጠፉህም ድረስ በዐንገትህ ላይ የብረት ቀንበር ይጭኑብሃል።


“ጠላቶችህ ከበው በሚያስጨንቁህ ጊዜ፥ ከሥቃይ የተነሣ፥ ጌታ እግዚአብሔር የሰጠህን፥ የሆድህ ፍሬ የሆኑትን የወንዶችና የሴቶች ልጆችህን ሥጋ ትበላለህ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች