Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 32:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እሳት ከቁጣዬ ትነድዳለች፤ እስከ ሲኦል ድረስ ታቃጥላለች፤ ምድርንም ከፍሬዋ ጋር ትበላለች፤ የተራሮችን መሠረትም ታነድዳለች።’”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 በቍጣዬ እሳት ተቀጣጥሏልና፤ እርሱ እስከ ሲኦል ዘልቆ ይነድዳል። ምድርን እስከ ሰብሏ ይበላል፤ የተራሮችንም መሠረት ያቀጣጥላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 በቊጣዬ እሳት ይቀጣጠላል፤ እስከ ሲኦል ጥልቀት ድረስ ይነዳል፤ ምድርንና ምርቱን ይበላል። ቃጠሎውም እስከ ተራራዎች መሠረት ድረስ ያቃጥላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 እሳት ከቍ​ጣዬ ትነ​ድ​ዳ​ለ​ችና፥ እስከ ሲኦል ድረስ ታቃ​ጥ​ላ​ለች፤ ምድ​ር​ንም ከፍ​ሬዋ፤ ጋር ትበ​ላ​ለች፤ የተ​ራ​ሮ​ችን መሠ​ረት ታነ​ድ​ዳ​ለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እሳት ከቁጣዬ ትነድዳለችና፥ 2 እስከ ሲኦል ድረስ ታቃጥላለች፥ 2 ምድርንም ከፍሬዋ ጋር ትበላለች፥ 2 የተራሮችን መሠረት ታነድዳለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 32:22
42 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ካፍ። እግዚአብሔር መዓቱን ፈጽሞአል፥ ጽኑ ቁጣውን አፍስሶአል፥ እሳትን በጽዮን ውስጥ አቃጠለ፥ መሠረትዋንም በላች።


የምታቃጥላችሁ እሳት ከቁጣዬ ትነድዳለችና ከጠላቶችህ ጋር ወደማታውቀው ምድር አሻግርሃለሁስ።”


ስለዚህ “ጠብቁኝ” ይላል ጌታ፤ ለመበዝበዝ እስከምነሣበት ቀን ድረስ፥ ፍርዴ ሕዝቦችን ለመሰብሰብ፥ መንግሥታትንም ለማከማቸት ነው፥ ይህም መዓቴንና የቁጣዬን ትኩሳት ሁሉ ለማፍሰስ ነው፤ በቅንዓቴ እሳት ምድርም ሁሉ ትበላለችና።


ተራሮች በሥሩ ይቀልጣሉ፥ ሸለቆዎችም በእሳት ፊት እንዳለ ሰም፥ ከቁልቁለት እንደሚወርድ ውኃ፥ ይሰነጠቃሉ።


አንተም የሰጠሁህን ርስት ትለቅቃለህ፥ በማታውቃትም ምድር ለጠላቶችህ ባርያ እንድትሆን አደርግሃለሁ፤ ለዘለዓለም የሚነድደውን እሳት በቁጣዬ አንድዳችኋልና።”


ጽኑ ፍቅርህ በእኔ ላይ ታላቅ ናትና፥ ነፍሴንም ከታችኛይቱ ሲኦል አድነሃታልና።


እሳትም ከጌታ ዘንድ ወጥቶ ያጥኑ የነበሩትን ሁለት መቶ ኀምሳ ሰዎች በላቸው።


አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና።


ነገር ግን እግዚአብሔርን የማያውቁትን፥ ለጌታችንም ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል፤


እናንተ እባቦች! የእፉኝት ልጆች! ከገሃነም ፍርድ እንዴት ታመልጣላችሁ?


ዓይንህ ካሰናከለህ አውጥተህ ጣለው፤ ሁለት ዐይን ኖሮህ ወደ ገሃነመ እሳት ከምትጣል፥ አንድ ዐይን ኖሮህ ወደ ሕይወት ብትገባ ይሻልሃል።


ሥጋን የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይችሉትን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንና ሥጋን በገሃነም ሊያጠፋ የሚችለውን እርሱን ፍሩ።


ተራሮች አንተን አይተው ተወራጩ፥ የውኃ ወጀብ አለፈ፥ ጥልቁም ድምፁን ሰጠ፥ እጁንም ወደ ላይ አነሳ።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያሳድዱአትና ይበዘብዙአት ዘንድ በልባቸው ሁሉ ደስታና በነፍሳቸው ንቀት ምድሬን ርስት አድርገው ለራሳቸው በሰጡ በቀሩት አሕዛብና በኤዶምያስ ሁሉ ላይ በቅንዓቴ እሳት ተናግሬአለሁ፤


ጋሜል። በጽኑ ቁጣው የእስራኤልን ቀንድ ሁሉ ቀጠቀጠ፥ ቀኝ እጁን ከጠላት ፊት ወደ ኋላ መለሰ፥ በዙሪያውም እንደሚባላ እንደ እሳት ነበልባል ያዕቆብን አቃጠለ።


እናንተም የይሁዳ ሰዎች በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሆይ! ስለ ሥራችሁ ክፋት ቁጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣ የሚያጠፋውም ሳይኖር እንዳያቃጥል፥ ለጌታ እራሳችሁን ግረዙ፥ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ።”


ተራሮች ይፈልሳሉ፥ ኮረብቶችም ይወገዳሉ፤ ቸርነቴ ግን ከአንቺ ዘንድ አይፈልስም የሰላሜም ቃል ኪዳን አይወገድም፥ ይላል የሚራራልሽ ጌታ።


ከቀድሞም ጀምሮ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅታለች፤ ለንጉሥም ተበጅታለች፤ ጥልቅና ሰፊም አድርጎአታል፤ እሳትና ብዙ ማገዶ ተከምሮአል፤ የጌታም እስትንፋስ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃጥለዋል።


ስለዚህ መርገም ምድርን ትበላለች፥ ነዋሪዎቿም ስለ ጥፋታቸው ይቀጣሉ፤ ስለዚህ የምድር ነዋሪዎች ይቃጠላሉ ጥቂት ሰዎችም ይቀራሉ።


አቤቱ፥ ሰማዮችህን ዝቅ ዝቅ አድርጋቸው ውረድም፥ ተራሮችን ዳስሳቸው ይጢሱም።


እሳት በፊቱ ይሄዳል፥ ጠላቶቹንም በዙሪያው ያቃጥላል።


አምላኬ ሆይ፥ እንደ ትቢያ በነፋስ ፊትም እንደ ገለባ አድርጋቸው።


አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው።


እጅህ ጠላቶችህን ሁሉ ታገኛቸዋለች፥ ቀኝህም የሚጠሉህን ሁሉ ታገኛቸዋለች።


ጌታ በእርሱ ላይ ቁጣውና ቅናቱ ይነድበታል እንጂ ለዚያ ሰው ፈጽሞ ይቅርታ አያደርግም። በዚህ መጽሐፍ የተጻፈው ርግማን ሁሉ ይወርድበታል፤ ጌታ ስሙን ከሰማይ በታች ይደመስሰዋል።


ጉልበታችሁም በከንቱ ያልቃል፤ ምድራችሁም የተትረፈረፈውን ምርትዋን አትሰጥም፥ የምድሪቱም ዛፎች ፍሬያቸውን አይሰጡም።


እነርሱም የእነርሱም የሆነው ሁሉ በሕይወታቸው ሳሉ ወደ ሲኦል ወረዱ፤ ምድሪቱም በእነርሱ ላይ ተዘጋችባቸው፥ ከጉባኤውም መካከል ጠፉ።


በቅንዓቴና በቁጣዬ እሳት ተናግሬአለሁ፦ በዚያ ቀን በእስራኤል ምድር ጽኑ መናወጥ ይሆናል፤


ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ አሳየኝ፤ እነሆም፥ ጌታ እግዚአብሔር በእሳት ለመፍረድ ጠራ፤ እርሷም ታላቁን ቀላይና ምድርን በላች።


ቤት። ጌታ የያዕቆብን ማደሪያዎች ሁሉ ዋጠ፥ አልራራምም፥ በመዓቱ የይሁዳን ሴት ልጅ አምቦች አፈረሰ፥ ወደ ምድርም አወረዳቸው መንግሥቱንና አለቆችዋን አረከሰ።


ዳሌጥ። ቀስቱን እንደ ጠላት ገተረ፥ እንደ አስጨናቂ ቀኝ እጁን አጸና፥ ለዓይንም የሚያምረውን ሁሉ ገደለ፥ በጽዮን ሴት ልጅ ድንኳን መዓቱን እንደ እሳት አፈሰሰ።


ነገር ግን በቁጣ ተነቀለች፥ ወደ መሬትም ተጣለች፤ የምሥራቅ ነፋስ ፍሬዋን አደረቀ፤ ብርቱ ቅርንጫፎቿም ተሰበሩና ደረቁ፤ እሳትም በላቸው።


እሰበስባችሁአለሁ፥ የመዓቴንም እሳት አነድባችኋለሁ በውስጡም ትቀልጣላችሁ።


በዮሴፍ ቤት ላይ እንደ እሳት በድንገት እንዳይቀጣጠል፥ በቤቴልም ላይ የሚያጠፋው ሳይኖር እንዳይበላት፥ ጌታን ፈልጉ፥ በሕይወትም ትኖራላችሁ።


በጌታ የመዓት ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች፥ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ አስፈሪ ፍፃሜ ያመጣባቸዋልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች