Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 32:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 “በምድረ በዳ በጥማት፥ የነፋስ ጩኸትም በሞላበት በምድረ በዳ አገኘው፥ መከታ ሆነለት፥ ተጠነቀቀለትም፥ እንደ ዐይን ብሌኑም ጠበቀው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እርሱን በምድረ በዳ፣ ባዶና ጭው ባለ በረሓ ውስጥ አገኘው፤ ጋሻ ሆነው፤ ተጠነቀቀለትም፤ እንደ ዐይኑ ብሌን ጠበቀው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 “በነፋሻማ ባዶ በረሓ በምድረ በዳ አገኘው፤ መከታ ሆነለት፤ ጠበቀውም፤ እንደ ዐይን ብሌኑም ተንከባከበው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በም​ድረ በዳ አጠ​ገ​ባ​ቸው፤ በጥ​ማ​ትና በድ​ካም ቦታ፥ በው​ድማ ከበ​ባ​ቸው፤ መገ​ባ​ቸው፤ መራ​ቸ​ውም፤ እንደ ዐይን ብሌ​ንም ጠበ​ቃ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በምድረ በዳ በጥማት፥ 2 የነፋስ ጩኸትም በሞላበት ውድማ አገኘው፤ 2 ከበበው ተጠነቀቀለትም፤ 2 እንደ ዓይን ብሌን ጠበቀው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 32:10
25 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በመኰንኖችም ላይ ውርደትን ዘረገፈ፥ መንገድም በሌለበት በምድረ በዳ አንከራተታቸው።


እንደ ዐይን ብሌን ጠብቀኝ፥ በክንፎችህ ጥላ ሰውረኝ


ትእዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ትኖራለህ፥ ሕጌንም እንደ ዓይንህ ብሌን ጠብቅ፥


በውድዋ ላይ ተደግፋ ከምድረበዳ የምትወጣ ይህች ማን ናት? ከእንኮይ በታች አስነሣሁህ፥ በዚያ እናትህ ወለደችህ፥ በዚያም ወላጅ እናትህ አማጠችህ።


በጭንቃቸው ሁሉ እርሱ ተጨነቀ፥ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤ በፍቅሩና በርኅራኄውም ተቤዣቸው፥ በቀደመውም ዘመን ሁሉ አንሥቶ ተሸከማቸው።


መታጠቂያ በሰው ወገብ ላይ እንደሚጣበቅ፥ እንዲሁ ሕዝብና ስም፥ ምስጋናና ክብር እንዲሆኑልኝ የእስራኤልን ቤት ሁሉ የይሁዳንም ቤት ሁሉ ከእኔ ጋር አጣብቄአለሁ፥ ይላል ጌታ፤ ነገር ግን አልሰሙም።”


በመንገድ በመራሽ ጊዜ ጌታ አምላክሽን በመተው በራስሽ ላይ ይህን አላመጣሽምን?


እነርሱም፦ ‘ከግብጽ ምድር ያወጣን፥ በምድረ በዳም በባድማ ጉድጓድም ባለበት ምድር፥ በውኃ ጥምና በሞት ጥላ ምድር፥ ማንም በማያልፍበትና ማንም በማይቀመጥበት ምድር የመራን ጌታ ወዴት አለ?’ አላሉም።


አዝኖልሽ ከእነዚህ ነገሮች አንዱን እንኳ ሊያደርግልሽ አንድም ዐይን አልራራልሽም፥ ነገር ግን በተወለድሽበት ቀን ሰውነትሽ የተጠላ ስለ ነበር በሜዳ ላይ ተጣልሽ።


በግብጽ ምድረ በዳ ከአባቶቻችሁ ጋር እንደ ተፋረድሁ እንዲሁ ከእናንተ ጋር እፋረዳለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


እኔም ኤፍሬምን ክንዱን ይዤ መራመድን አስተማርሁት፤ እኔም እፈውሳቸው እንደ ነበርሁ አላወቁም።


በምድረ በዳ፥ እጅግ በደረቀ ምድር አውቄህ ነበር።


የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ ከክብሩ በኋላ ወደ ዘረፏችሁ አሕዛብ ልኮኛል፥ የሚነካችሁ በቀጥታ እኔን የዓይኔን ብሌን ይነካል።


“ሩጥ፥ ይህንም ጎልማሳ እንዲህ በለው፦ ኢየሩሳሌም በውስጥዋ ካሉት ሰዎችና እንስሶች ብዛት የተነሣ ቅጥር እንደሌላቸው መንደሮች ትሆናለች።


ፈቃዱንም ካወቅህ፥ ሕግም ስለተማርህ የሚሻለውን ከወሰድህ፥


በማንኛውም መንገድ ጥቅሙ ብዙ ነው። አስቀድሞ የእግዚአብሔር ቃላት አደራ ተሰጣቸው።


“ከኮሬብም ወጣን፥ ጌታ አምላካችን እንዳዘዘን በታላቁ እጅግም በሚያስፈራ በዚያ ሁሉ ባያችሁት ምድረ በዳ በኩል በተራራማው በአሞራውያን መንገድ ሄድን፥ ወደ ቃዴስ በርኔም መጣን።


ወደዚህም ስፍራ እስክትመጡ ድረስ በሄዳችሁበት መንገድ ሁሉ፥ በምድረ በዳም፥ ሰው ልጁን እንደሚንከባከብ፥ ጌታ አምላካችሁ እንዴት እንደተንከባከባችሁ አይታችኋል።’


ያስተምራችሁ ዘንድ ከሰማይ ድምፁን አሰማችሁ፥ በምድርም ላይ ታላቁን እሳቱን አሳያችሁ፥ ከእሳቱም መካከል የእርሱን ድምፅ ሰማችሁ።።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች