Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 31:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ጌታ ራሱ በፊትህ ይሄዳል፤ ከአንተም ጋር ይሆናል፤ ፈጽሞ አይለይህም፤ አይተውህምም፤ አትፍራ፤ ተስፋም አትቁረጥ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እግዚአብሔር ራሱ በፊትህ ይሄዳል፤ ከአንተም ጋራ ይሆናል፤ ፈጽሞ አይለይህም፤ አይተውህምም፤ አትፍራ፤ ተስፋም አትቍረጥ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ራሱ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር በመሆን ይመራሃል፤ አይጥልህም ከቶም አይተውህም፤ ስለዚህ አትፍራ፤ ተስፋም አትቊረጥ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በፊ​ት​ህም የሚ​ሄድ እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ከአ​ንተ ጋር ይሆ​ናል፤ አይ​ጥ​ል​ህም፤ አይ​ተ​ው​ህም፤ አት​ፍራ፤ አት​ደ​ን​ግጥ’ ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በፊትህም የሚሄድ እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ ከአንተ ጋር ይሆናል፥ አይጥልህም፥ አይተውህም፤ አትፍራ፥ አትደንግጥ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 31:8
25 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርሱም “እኔ ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፥ ዕረፍትም እሰጥሃለሁ” አለው።


ብርቱና ደፋር ሁኑ፤ አትፍሯቸው ወይም አትደንግጡላቸው። ጌታ አምላክህም ካንተ ጋር ይሄዳልና፤ አይተውህም፤ አይጥልህምም።”


በምትሄድበት ሁሉ ጌታ አምላክህ ከአንተ ጋራ ነውና ጽና፥ አይዞህ፥ አትፍራ፥ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?”


እንግዲህ ስለ እነዚህ ነገሮች ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?


በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ማንም አይቋቋምህም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ነበርሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ አልጥልህም፥ አልተውህምም።


ዳዊትም ልጁን ሰሎሞንን እንዲህ አለው፦ “ጠንክር፥ አይዞህ፥ አድርገውም፤ አምላኬ እግዚአብሔር አምላክ ከአንተ ጋር ነውና አትፍራ፥ አትደንግጥም፥ ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት የሚሆነው ሥራ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ እርሱ አይተውህም፥ አይጥልህምም።


እንደሚበላ እሳት ሆኖ በፊትህ ዛሬ የሚያልፈው ጌታ እግዚአብሔር መሆኑን እወቅ፥ እርሱ ያጠፋቸዋል፥ በፊትህም ያዋርዳቸዋል፤ ጌታ ተስፋ እንደሰጠህ አንተም ታሳድዳቸዋለህ፥ በፍጥነትም ታጠፋቸዋለህ።


ጌታ አምላክህም ራሱ በፊትህ ቀድሞ ይሄዳል፤ እነዚህንም አሕዛብ ከፊትህ ያጠፋቸዋል፤ አንተም ምድራቸውን ትወርሳለህ፤ ጌታ እንደ ተናገረው ኢያሱም አንተን ቀድሞ ይሻገራል።


ሕይወታችሁ ከፍቅረ ንዋይ የጸዳ ይሁን፤ ነገር ግን እርሱ ራሱ “አልለቅህም፤ ከቶም አልተውህም፤” ብሎአልና ያላችሁ ይብቃችሁ።


እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ በምትሄድባትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፥ ወደዚችም ምድር እመልስሃለሁ፥ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና።”


ጌታ እግዚአብሔር መሐሪ አምላክ ነውና አይተዋችሁም፥ አያጠፋችሁምም፤ ለአባቶቻችሁ የገባውን ቃል ኪዳኑን አይረሳም።


“ከግብጽ ያወጣህ አምላክህ ጌታ ከአንተ ጋር ነውና፥ ጠላቶችህን ለመውጋት ወደ ጦርነት ስትሄድ፥ ሠረገሎችንና ፈረሶችን ከአንተ የሚበልጥ ሠራዊትንም በምታይበት ጊዜ አትፍራቸው።


አገልጋዬ ዳዊት እንዳደረገው በፍጹም ልብህ ብትታዘዘኝ፥ በሕጎቼና በትእዛዞቼ ጸንተህ ብትኖር፥ በእኔ ፊት ሞገስ ብታገኝ፥ እኔ ዘወትር ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ በእስራኤል ላይ እንድትነግሥም አደርግሃለሁ፤ ለዳዊት ባደረግሁት ዓይነት ዘሮችህ ከአንተ በኋላ እንደሚነግሡ አረጋግጥልሃለሁ።


ለእነርሱም ከማደርገው በጎነት አልመለስም ስል፥ ከእነርሱ ጋር የዘለዓለምን ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ ከእኔም ዘንድ ፈቀቅ እንዳይሉ መፈራቴን በልባቸው ውስጥ አኖራለሁ።


ሕዝቡ ሙሴ ከተራራው ሳይወርድ እንደ ዘገየ ባዩ ጊዜ፥ ወደ አሮን ተሰብስበው፦ “ይህ ከግብጽ ምድር ያወጣን ሰው ሙሴ ምን እንደ ደረሰበት አናውቅም፤ ስለዚህ ተነሥና በፊታችን የሚሄዱ አማልክት ሥራልን” አሉት።


ከብንያም ነገድ የራፉ ልጅ ፈልጢ፤


ጌታም ለነዌ ልጅ ለኢያሱ፥ “በርታ፤ ደፋር ሁን፤ የእስራኤልን ልጆች በመሐላ ቃል ወደ ገባሁላቸው ምድር ታስገ ባቸዋለህና፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ” በማለት ትእዛዝ ሰጠው።


ጌታ የራሱ ሕዝብ ሊያደርጋችሁ ስለ ወደደ፥ ስለ ታላቅ ስሙ ሲል ጌታ ሕዝቡን አይተውም።


በእስራኤል ልጆች መካከል አድራለሁ፤ ሕዝቤን እስራኤልንም ከቶ አልለያቸውም።”


አምላካችን እግዚአብሔር ከቀድሞ አባቶቻችን ጋር እንደ ነበረ ሁሉ ከእኛ ጋርም ይኑር፤ ምንጊዜም፤ አይተወንም፤ አይጥለንም፤


ጌታ ስለ እስራኤል ሙሴን ያዘዘውን ሥርዓትና ፍርድ ለመፈጸም ብትጠነቀቅ በዚያን ጊዜ ይከናወንልሃል፤ አይዞህ፥ በርታ፤ አትፍራ፥ አትደንግጥ።


ጌታ ሕዝቡን አይጥልምና፥ ርስቱንም አይተውምና


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች