ዘዳግም 29:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 እዚህ የቆምኸው ጌታ ዛሬ ከአንተ ጋር ወደሚያደርገውና በመሓላ ወደሚያጸናው ኪዳን ከጌታህ ከእግዚአብሔር ጋር ትገባ ዘንድ፥ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 እዚህ የቆምኸው እግዚአብሔር ዛሬ ከአንተ ጋራ ወደሚያደርገውና በመሐላ ወደሚያጸናው ኪዳን ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ጋራ ትገባ ዘንድ፣ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 የቆማችሁትም ከአምላካችሁ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ለመግባት ነው፤ ይህም ቃል ኪዳን እግዚአብሔር አምላካችሁ ዛሬ ለእናንተ በመሐላ ያረጋገጠው ነው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 ይኸውም አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ዛሬ በሚያደርገው ቃል ኪዳንና አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር በተማማለው መሐላ ትገባ ዘንድ ነው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12-13 ይኸውም ዛሬ ለእርሱ ሕዝብ አድርጎ ያስነሣህ ዘንድ፥ እርሱም ለአንተ እንደ ተናገረ ለአባቶችህም ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም እንደ ማለ አምላክ ይሆንልህ ዘንድ፥ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ዛሬ በሚያደርገው ቃል ኪዳን ትገባ ዘንድና የአምላክህን የእግዚአብሔርን መሐላ ትሰማ ዘንድ ነው። ምዕራፉን ተመልከት |