ዘዳግም 28:54 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)54 በመካከልህ በጣም ደግና ርኅሩኅ የሆነው ሰው እንኳ ለገዛ ወንድሙ፥ አቅፋውም ለምትተኛ ለሚስቱ፥ ወይም ለተረፉት ልጆቹ አይሳሳም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም54 ሌላው ይቅርና በመካከልህ በጣም ደግና ርኅሩኅ የሆነው ሰው እንኳ ለገዛ ወንድሙ ወይም ለሚወድዳት ሚስቱ ወይም ለተረፉት ልጆቹ አይራራላቸውም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም54 በመካከላችሁ በመለሳለስና በቅምጥልነት በትውልዱም በመመካት የሚኖረው ሰው እንኳ ለወንድሙ፥ ዐቅፋው ለምትተኛው ሚስቱና ከጥፋት ለተረፉት ልጆቹ ከዚያ ምግብ ለመስጠት ይሰስታል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)54 በአንተ ዘንድ የተደላደለና የተቀማጠለ ሰው በወንድሙ፥ አብራውም በምትተኛ በሚስቱ፥ በቀሩትም ልጆቹ ይቀናል፤ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)54 በአንተ ዘንድ የተለሳለሰና በቅምጥልነት ሁልጊዜ ይኖር የነበረ ሰው በወንድሙ፥ አቅፋውም በምትተኛ በሚስቱ፥ በቀሩትም ልጆች ይቀናል፤ ምዕራፉን ተመልከት |