Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 27:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 “‘በጌታ ዘንድ የተጠላ የሠራተኛ እጅ ሥራን የተቀረጸ ወይም ቀልጦ የተሠራ ምስልን የሚያደርግ፥ በስውርም የሚያቆመው ሰው የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 “የእጅ ጥበብ ባለሙያ የሠራውን፣ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ የሆነውን ምስል የሚቀርጽ ወይም ጣዖትን የሚያበጅ፣ በስውርም የሚያቆም ሰው የተረገመ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 “ ‘እንጨት ጠርቦ፥ ድንጋይ አለዝቦ፥ ብረት አቅልጦ ጣዖት በመሥራት በስውር የሚሰግድለት ማንኛውም ሰው የተረገመ ይሁን! እግዚአብሔር የጣዖት አምልኮን ይጠላል።’ “ሕዝቡም ሁሉ ሲመልሱ ‘አሜን!’ ይበሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ጠላ የሠ​ራ​ተኛ እጅ ሥራን፥ የተ​ቀ​ረፀ ወይም ቀልጦ የተ​ሠራ ምስ​ልን የሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በስ​ው​ርም የሚ​ያ​ቆ​መው ሰው ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ መል​ሰው አሜን ይላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ የሠራተኛ እጅ ሥራን የተቀረጸ ወይም ቀልጦ የተሠራ ምስልን የሚያደርግ፥ በስውርም የሚያቆመው ሰው ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ መልሰው አሜን ይላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 27:15
44 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቀልጠው የተሠሩ የአማልክት ምስሎች ለአንተ አታድርግ።


በላይ በሰማያት ካለው፥ በታች በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም አምሳል፥ የተቀረጸ ምስል ለአንተ አታድርግ።


“ ‘በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፥


“እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝና ለራሳችሁ ይሆኑ ዘንድ ጣዖታትን አትሥሩ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ለእርሱም ለመስገድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ።


ወደ ጣዖታትም ዘወር አትበሉ፥ ለራሳችሁም ይሆኑ ዘንድ ቀልጠው የተበጁትን የአማልክት ምስሎች አትሥሩ፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።


እንዲህማ ካልሆነ፥ በመንፈስ በምትባርክበት ጊዜ፥ አንተ የምትለውን የማያውቅ እንግዳ ሰው ካልተረዳ፥ እንዴት አድርጎ ለምስጋናህ፥ “አሜን” ሊል ይችላል?


ከእኔ ጋር የብር አማልክትን አትሥሩ፥ የወርቅ አማልክትንም ለእናንተ አትሥሩ።


ጌታም ከእስራኤል ልጆች ፊት እንዳወጣቸው እንደ አሕዛብ ያለ ርኩሰት በጌታ ፊት ክፉ ነገር አደረገ።


እንዲሁም ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ከርኲሰት ተራራ በስተ ደቡብ ዐስታሮት ተብላ ለምትጠራው ለሲዶና አምላክ፥ ከሞሽ ተብሎ ለሚጠራው ለሞዓብ አምላክና ሞሌክ ተብሎ ለሚጠራው ለዐሞን አምላክ ንጉሥ ሰሎሞን አሠርቶአቸው የነበሩት አጸያፊዎች ምስሎች ሁሉ የረከሱ መሆናቸውን አስገነዘበ።


ነገር ግን የይሁዳ ሰዎችም ቢሆኑ፥ አምላካቸው እግዚአብሔር የሰጣቸውን ትእዛዞች አልጠበቁም ነበር፤ እነርሱም የእስራኤል ሕዝብ የተቀበሉትን ልማድ ተከታዮች ነበሩ።


አሁንም ንጉሥ ጌታዬ የባርያውን ቃል ያድምጥ፤ ጌታ በእኔ ላይ አነሣሥቶህ እንደሆነ፥ መሥዋዕት ይቀበል፤ ነገር ግን ይህን ያደረጉት ሰዎች ከሆኑ፥ በጌታ ፊት የተረገሙ ይሁኑ፥ ‘ሂድ ሌሎችን አማልክት አምልክ’ ብለው በጌታ ርስት ድርሻ እንዳይኖረኝ ዛሬ አሳደውኛልና።


በመካከላቸውም አስጸያፊ ምስሎቻቸውንና የዕንጨትና የድንጋይ፥ የብርና የወርቅ ጣዖቶቻቸውን አይታችኋል።


እርግማንንም የሚያመጣው ይህ ውኃ ወደ ሆድሽ ይግባ፥ ሆድሽንም ይንፋው፥ ጭንሽንም ያሰልስለው፤’ ሴቲቱም፦ ‘አሜን አሜን’ ትላለች።


ራሔልም ተራፊምን ወስዳ ከግመል ኮርቻ በታች ሸሸገች፥ በላዩም ተቀመጠችበት። ላባም ድንኳኑን ሁሉ ፈለገ፥ አንዳችም አላገኘም።


ላባም በጎቹን ለመሸለት ሄዶ ነበር፥ ራሔልም የአባትዋን ቤት ጣዖቶች ሰረቀች።


እንዲህም አለ፦ “ከነዓን የተረገመ ይሁን! ለወንድሞቹም የባርያዎች ባርያ ይሁን።”


የጌጦቻቸውን ውበት ወደ ትዕቢት ለወጡ፥ የርኩሰታቸውን ምስሎችና አስከፊ ነገሮችን ሰሩባቸው፥ ስለዚህ እኔም ይህንን ለእነርሱ ርኩስ ነገር አደርገዋለሁ።


ነቢዩም ኤርምያስ እንዲህ አለ፦ “አሜን፥ ጌታ እንዲህ ያድርግ፤ የጌታን ቤት ዕቃዎችና ምርኮውን ሁሉ ከባቢሎን ወደዚህ ስፍራ በመመለስ ጌታ የተናገርኸውን የትንቢት ቃላት ይፈጽም።


ሰው በስውር ቦታ ቢሸሸግ፥ እኔ አላየውምን? ይላል ጌታ። ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን? ይላል ጌታ።


ይህ ዛሬ እንደሆነ ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ለአባቶቻችሁ እንድሰጣቸው የማልሁትን መሐላ እንዳጸና ነው።” እኔም፦ “አቤቱ! አሜን” ብዬ መለስሁለት።


እንደዚህም በላቸው፦ የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ የዚህን ቃል ኪዳን ቃላት የማይሰማ ሰው ርጉም ይሁን፥


በልቡም ማንም አያስብም፦ “ግማሽዋን በእሳት አቃጥያለሁ፥ በፍምዋም ላይ እንጀራን ጋግሬአለሁ፥ ሥጋም ጠብሼ በልቻለሁ፤ የቀረውንም አስጸያፊ ነገር አደርጋለሁን? ለዛፍስ ግንድ እሰግዳለሁን?” ለማለት እንኳን እውቀትና ማስተዋል የለውም።


የቀረውንም እንጨት አምላክ አድርጎ ምስል ይቀርጽበታል፤ በፊቱም ተጐንብሶ ይሰግድበታል፤ ወደ እርሱም እየጸለየ፦ አምላኬ ነህና አድነኝ ይላል።


“ስለዚህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋት ርኩሰት በተቀደሰው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፤


ከክፉ አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን።’


ስለዚህ ተናገራቸው፥ እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ማንም ሰው ከእስራኤል ቤት ጣዖቶቹን በልቡ የሚያኖር፥ የበደሉንም የማሰናከያ ድንጋይ በፊቱ የሚያቆም፥ ወደ ነቢዩም የሚመጣ፥ እኔ ጌታ እንደ ጣዖታቱ ብዛት እመልስለታለሁ።


ሌዋውያን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ብለው ይናገሩ፦


ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም፥ የእስራኤል አምላክ ጌታ ይባረክ።” ሕዝቡም ሁሉ “አሜን” አሉ፤ ጌታንም አመሰገኑ።


“ልጆችን የልጅ ልጆችንም በወለዳችሁ ጊዜ፥ በምድሪቱም ብዙ ዘመን በተቀመጣችሁ ጊዜ፥ ማናቸውም ቅርጽ የተቀረጸውን ምስል አድርጋችሁ ከረከሳችሁ፥ ታስቆጡትም ዘንድ በጌታ በአምላካችሁ ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ከሠራችሁ፥


የተቀረጸውንም የአምላኮቻቸውን ምስል በእሳት ታቃጥላለህ፤ በእነርሱ ላይ የተለበጠውን ብር ወይም ወርቅ አትመኝ፥ በጌታ አምላካችሁም ዘንድ ርኩስ ነውና እንዳትጠመድበት ከእርሱ ምንም አትውሰድ።


አንድ ሺህ አንድ መቶውን ሰቅል ብር በመለሰላት ጊዜ፥ እናቱ “ብሬን የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ጣዖት ለማበጀት ስለ ልጄን ለጌታ እቀድሰዋለሁ፤ አሁንም ለአንተው መልሼ እሰጥሃለሁ” አለችው።


ስለዚህ ብሩን ለእናቱ መለሰላት፤ እናቱም ከላዩ ሁለት መቶ ጥሬ ብር ወስዳ ለብር አንጥረኛ ሰጠች፤ አንጥረኛውም የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ጣዖት አደረገው፤ ምስሎቹም በሚካ ቤት ተቀመጡ።


ጠራቢው ገመድ ይዘረጋል፥ በጠመኔም ምልክት ያኖራል፥ በመሮም ይቀርጸዋል፥ በመለኪያም ይለከዋል፤ በቤትም ውስጥ እንዲቀመጥ በሰው አምሳልና በሰው ውበት ይቀርጸዋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች