Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 26:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ከቅዱስ ማደሪያህ ከሰማይ ወደ ታች ተመልከት፤ ሕዝብህን እስራኤልንና ለእኛ የሰጠኸንን ይህችን ማርና ወተት የምታፈሰውን ምድር ለአባቶቻችን በቃልህ እንደገባኸው መሓላ መሠረት ባርክ።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከቅዱስ ማደሪያህ ከሰማይ ተመልከት፤ ሕዝብህን እስራኤልንና ለአባቶቻችን በመሐላ ቃል በገባኸው መሠረት፣ ለእኛ የሰጠኸንን ይህችን ማርና ወተት የምታፈስሰውን ምድር ባርክ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 በሰማይ ካለው ቅዱስ መኖሪያህ ሆነህ ወደ ታች ተመልከት፤ ሕዝብህን እስራኤልንም ባርክ፤ ለቀድሞ አባቶቻችን በገባኸው ቃል መሠረት የሰጠኸንን በማርና በወተት የበለጸገችውን ለም ምድር ባርክ።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ከቅ​ዱስ ማደ​ር​ያህ ከሰ​ማይ ጐብኝ፤ ሕዝ​ብ​ህ​ንም እስ​ራ​ኤ​ልን፥ ወተ​ትና ማር የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር ትሰ​ጠን ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን እንደ ማል​ህ​ላ​ቸው የሰ​ጠ​ሃ​ቸ​ው​ንም ምድር ባርክ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ከቅዱስ ማደሪያህ ከሰማይ ጐብኝ፥ ሕዝብህንም እስራኤልን ለአባቶቻችን እንደ ማልህላቸው የሰጠኸንንም ወተትና ማር የምታፈስሰውን አገር ባርክ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 26:15
26 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከሰማይ ተመልከት፥ ከቅዱስነትህና ከክብርህም ማደሪያ ጐብኝ፤ ቅንዓትህና ኃይልህስ ወዴት ነው? ለእኔም የሆነው የልብህ ናፍቆትና ርኅራኄህ ለእኔ ተከለከለ?


እነሆ፥ እጄን በላያቸው ላይ አነሣለሁ፥ በምርኮ ተገዝተውላቸው ለነበሩት ራሳቸው በምርኮ ይዘረፋሉ፤ የሠራዊት ጌታም እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።


የእስራኤል አምላክ የሠርዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ምርኮአቸውን በመለስሁ ጊዜ በይሁዳ አገር በከተሞችዋ፦ ‘የጽድቅ ማደሪያ ሆይ! የቅድስና ተራራ ሆይ! ጌታ ይባርክህ’ የሚልን ቃል እንደገና ይናገራሉ።


አንተ ጸሎቱን ስማ፤ ሕዝብህ እስራኤላውያን እንደሚያደርጉት በመላው ዓለም የሚኖሩ ሕዝቦች አንተን በማወቅ እንዲታዘዙህና እንዲያከብሩህ አድርግ፤ በምትኖርበት በሰማይ ሆነህ የዚህን ሰው ጸሎት ስማ፤ እንድታደርግለት የሚለምንህንም ሁሉ ፈጽምለት፤ ይህም በሚሆንበት ጊዜ ይህ እኔ የሠራሁት ቤተ መቅደስ የአንተ ስም የሚጠራበት መሆኑን ያውቃሉ።


“በውኑ እግዚአብሔር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ ሰማያት፥ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ሊይዝህ አይችልም፤ እኔ የሠራሁት ይህ ቤተ መቅደስማ ምንኛ ያንስ!


ስለዚህ እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ፦ ‘በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ! ስምህ ይቀደስ፤


የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ ጌታ ቀብቶኛልና፥ ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፥ ለተማረኩትም ነጻነትን፥ ለታሰሩትም መፈታትን እንዳውጅ ልኮኛል።


ለዘለዓለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፥ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል፦ የተዋረዱትን ሰዎች መንፈስ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠውንም ልብ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ።


የጌታ አምላካችን ቸርነት በላያችን ይሁን። የእጆቻችንንም ሥራ በላያችን አቅና።


መሥዋዕትን ብትወድድስ በሰጠሁህ ነበር፥ የሚቃጠለውም መሥዋዕት ደስ አያሰኝህም።


ሕዝብህን አድን፥ ርስትህንም ባርክ፥ ጠብቃቸው፥ ለዘለዓለሙም ከፍ ከፍ አድርጋቸው።


ከዚያ በኋላ የአባቶቻችን አምላክ ወደ ሆነው ወደ ጌታ ጮኽን፤ ጌታም ጩኸታችንን ሰማ። ጉስቁልናችንን፥ ድካማችንንና መጨቆናችንን ተመለከተ።


ወደዚህም ስፍራም አስገብቶን ወተትና ማር የምታፈስሰውንም ይህችን ምድር ሰጠን።


በኀዘኔም ጊዜ ከተቀደሰው ክፍል ላይ ምንም አልበላሁም፤ ወይም ንጹህ ባልነበርኩ ጊዜ ያነሣሁትም ሆነ ለሙታን ያቀረብሁት መባ የለም፤ ለአምላኬ ጌታ ድምጽ ታዝዣለሁ፤ ያዘዝኸኝንም ሁሉ ፈጽሜአለሁ።


ካህናቱና ሌዋውያኑም ተነሥተው ሕዝቡን ባረኩ፤ ድምጻቸውም ተሰማ፥ ጸሎታቸውም ወደ ቅዱስ መኖሪያው ወደ ሰማይ ዐረገ።


ለእግዚአብሔር ተቀኙ ለስሙም ዘምሩ፥ ወደ ምድረ በዳ ለወጣም መንገድ አድርጉ፥ ስሙ ጌታ ነው፥ በፊቱም ደስ ይበላችሁ።


የዱር እርያ አረከሳት፥ የአገር አውሬም ተሰማራባት።


እነሆ፥ ምድሪቱን በፊታችሁ አኖራለሁ፥ ግቡ፥ ጌታ ለእነርሱ ከእነርሱም በኋላ ለዘራቸው ይሰጣት ዘንድ ለአባቶቻችሁ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም የማለላቸውንም ምድር ውረሱ።’


እንግዲህ፥ እስራኤል ሆይ፥ ስማ! መልካም እንዲሆንልህ፥ የአባቶችህም አምላክ ጌታ እንደ ተናገረ፥ ወተትና ማር በምታፈስሰው ምድር፥ እጅግ እንድትበዛ በጥንቃቄ ጠብቅ።


የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ እንግዲህ ተመለስ፥ ከሰማይ ተመልከት፥ እይም፥ ይህችንም የወይን ግንድ ጐብኝ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች