ዘዳግም 26:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 ከዚያ በኋላ ለጌታህ እግዚአብሔር እንዲህ በል፦ ‘ከቤቴ የተቀደሰውን ድርሻ ወስጄ በሰጠኸኝ ትእዛዝ መሠረት ለሌዋዊው፥ ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ሰጥቻለሁ። ከትእዛዝህ አልወጣሁም፤ አንዱንም አልረሳሁም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 ከዚያ በኋላ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር እንዲህ በል፤ “በሰጠኸኝ ትእዛዝ መሠረት የተቀደሰውን ክፍል ከቤቴ አውጥቼ ለሌዋዊው፣ ለመጻተኛው፣ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ሰጥቻለሁ። ከትእዛዝህ አልወጣሁም፤ አንዱንም አልረሳሁም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ከዚያም በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት እንዲህ በል፦ ‘ከቤቴ የተቀደሰውን ድርሻ ወስጄ ባዘዝከን ትእዛዞች ሁሉ መሠረት ለሌዋውያን፥ ለመጻተኞች፥ ለሙት ልጆችና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች ሰጥቼአለሁ፤ ከትእዛዞችህም አልተላለፍኩም፤ የዘነጋሁትም ነገር የለም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት እንዲህ በል፦ የተቀደሰውን ነገር ከቤቴ ለይች ለሌዋዊው፥ ለመጻተኛውም፥ ለድሀ-አደጉም፥ ለመበለቲቱም እንዳዘዝኸኝ ትእዛዝ ሁሉ ሰጥቼአለሁ፤ ትእዛዝህን ምንም አላፈረስሁም፤ አልረሳሁምም፤ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት እንዲህ በል፦ የተቀደሰውን ነገር ከቤቴ ወስጄ ለሌዋዊው ለመጻተኛውም ለድሀ አደጉም ለመበለቲቱም እንዳዘዝኽኝ ትእዛዝ ሁሉ ሰጥቼአለሁ፤ ትእዛዝህን ምንም አላፈረስሁም፥ አልረሳሁምም፤ ምዕራፉን ተመልከት |