Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 25:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የወንድሙም ሚስት በሽማግሌዎች ፊት ወደ እርሱ ቀርባ፥ የአንድ እግሩን ጫማ በማውለቅ በፊቱ ላይ ትትፋበትና ‘የወንድሙን ቤት በማይሠራ ሰው ላይ እንዲህ ያለው ድርጊት ይፈጸምበታል’ ትበል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የወንድሙም ሚስት በሽማግሌዎች ፊት ወደ እርሱ ቀርባ፣ የአንድ እግሩን ጫማ በማውለቅ በፊቱ ላይ ትትፋበትና “የወንድሙን ቤት በማይሠራ ሰው ላይ እንዲህ ያለው ድርጊት ይፈጸምበታል” ትበል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የሟቹ ሚስት በከተማይቱ መሪዎች ፊት ወደ እርሱ ትቅረብ፤ ከእግሩ ጫማዎች አንዱን አውልቃ ምራቋን በፊቱ ላይ በመትፋት ‘ለወንድሙ ዘር ለመተካት እምቢ ለሚል ሰው ይህን ዐይነት አሳፋሪ ነገር ሊፈጸምበት ይገባል’ ትበል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ዋር​ሳ​ዪቱ በሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎቹ ፊት ወደ እርሱ ቀርባ፦ ‘የወ​ን​ድ​ሙን ቤት በማ​ይ​ሠራ ሰው ላይ እን​ዲህ ይደ​ረ​ግ​በ​ታል’ ስትል የአ​ንድ እግ​ሩን ጫማ ታውጣ፤ በፊ​ቱም እን​ትፍ ትበ​ል​በት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ዋርሳይቱ በሽማግሌዎቹ ፊት ወደ እርሱ ቀርባ፦ የወንድሙን ቤት በማይሠራ ሰው ላይ እንዲህ ይደረግበታል ስትል ጭማውን ከእግሩ ታውጣ፥ በፊቱም እንትፍ ትበልበት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 25:9
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አባትዋ ምራቁን በፊትዋ ቢተፋባት እንኳ እርሷ ሰባት ቀን ልታፍር አይገባትምን? ሰባት ቀን ከሰፈሩ ውጪ ተዘግቶባት ትቀመጥ፥ ከዚያም በኋላ ትመለስ።”


ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ነው፤ እኔ የጫማውን ጠፍር ልፈታ የተገበሁ አይደለሁም” አላቸው።


ያፌዙበታል፤ ይተፉበታል፥ ይገርፉታል፥ ከዚያም ይገድሉታል፤ እርሱ ግን ከሦስት ቀን በኋላ ይነሣል።”


ስብከቱም፥ “እኔ ጐንበስ ብዬ የጫማውን ማሰሪያ መፍታት ከማይገባኝ፥ ከእኔ የሚበልጥ ከእኔ በኋላ ይመጣል፤


ተፉበት፤ መቃውንም ነጥቀው ራሱን መቱት።


በዚያን ጊዜ ፊቱ ላይ ተፉበት፥ መቱት፥ በጥፊም መቱት


ጀርባዬን ለገራፊዎች፥ ጉንጬንም ለጠጉር ነጪዎች ሰጠሁ፤ ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስሁም።


በዚያ ጊዜ ጌታ የዓሞጽን ልጅ ኢሳይያስን፥ “ሂድ፥ ማቅህን ከወገብህ አውርድ፤ ጫማህንም ከእግርህ አውልቅ” ብሎ ተናገረው። እንደተባለውም አደረገ፤ ራቁቱን ሆኖ በባዶ እግሩም ሄደ።


ተጸየፉኝ፥ ከእኔም ራቁ፥ አክታቸውንም በፊቴ መትፋትን አልተዉም።


ስለዚህ የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በእውነት ቤትህ፥ የአባትህም ቤት ለዘለዓለም በፊቴ እንዲኖር ተናግሬአለሁ፤’ አሁን ግን ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ ከእኔ ይራቅ።


ከዚያም የከተማው ሽማግሌዎች ሰው ጠርተው ያነጋግሩት፤ እርሱም፥ ‘እርሷን ላገባት አልፈልግም’ ብሎ በሐሳቡ ቢጸና፥


የዚያም ሰው የዘር ሐረግ በእስራኤል ዘንድ፥ ‘ጫማው የወለቀበት ቤት’ ተብሎ ይታወቃል።


የቅርብ ዘመዱም፦ “የራሴን ርስት እንዳላበላሽ መውሰድ አልችልም፥ እኔ የራሴ ላደርገው አልችልምና አንተ እንድትወስደው ፈቅጄልሃለሁ” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች