Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 24:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 የወይን ተክልህን ፍሬ ስትሰበስብ ቃርሚያውን ለመሰብሰብ አትመለስበት፤ የቀረውን ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ተወው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 የወይን ተክልህን ፍሬ ስትሰበስብ ቃርሚያውን ለመሰብሰብ አትመለስበት፤ የቀረውን ለመጻተኛው፣ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ተወው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 የወይንህንም ዘለላ በምትሰበስብበት ጊዜ የቀረውን ፍሬ ለመውሰድ ወደ ወይኑ ሐረግ ዳግመኛ አትመለስ፤ የቀሩትን ዘለላዎች ለመጻተኞች፥ ወላጆቻቸው ለሞቱባቸው ልጆችና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች ተውላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የወ​ይ​ን​ህን ፍሬ በቈ​ረ​ጥህ ጊዜ ቃር​ሚ​ያ​ውን አት​ል​ቀ​መው፤ ለመ​ጻ​ተ​ኛና ለድሃ-አደግ፥ ለመ​በ​ለ​ትም ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 የወይንህን ፍሬ በቈረጥህ ጊዜ ቃርሚያውን አትልቀመው፤ ለመጻተኛና ለድሀ አደግ ለመበለትም ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 24:21
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሌቦች ቢመጡብህ ወይም ወንበዴዎች በሌሊት ቢመጡ፥ የሚበቃቸውን ብቻ ይሰርቁ የለምን? ወይንንም የሚቆርጡ ወደ አንተ ቢመጡ ቃርሚያ ያስቀሩ የለምን? አንተ ግን ምንኛ ጠፋህ!


“የዕርሻህን ሰብል በምታጭድበት ጊዜ፥ ተረስቶ የቀረ ነዶ ቢኖር፥ ያን ለመውሰድ ተመልሰህ አትሂድ። ጌታ እግዚአብሔር በእጅህ ሥራ ሁሉ እንዲባርክህ ነዶውን ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ተወው።


የወይራ ዛፍህን ፍሬ በምታራግፍበት ጊዜ በየቅርንጫፉላይ የቀረውን ለመቃረም ተመልሰህ አትሂድ፤ ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ተወው።


በግብጽ ባርያ እንደ ነበርህ አስታውስ፤ ስለዚህ ይህን ታደርግ ዘንድ አዝዤሃለሁ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች