Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 21:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ወደ ቤትህ ውሰዳት፤ ጠጉሯን ትላጭ፤ ጥፍሯንም ትቆረጥ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ወደ ቤትህ ውሰዳት፤ ጠጕሯን ትላጭ፤ ጥፍሯንም ትቍረጥ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ይህም ከሆነ፥ እርስዋን ወደ ቤትህ ወስደህ፥ ራስዋን ተላጭታ፥ ጥፍርዋን ተቈርጣ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ወደ ቤትህ ታመ​ጣ​ታ​ለህ፤ ራስ​ዋ​ንም ትላ​ጫ​ታ​ለህ፤ ጥፍ​ር​ዋ​ንም ትቈ​ር​ጥ​ላ​ታ​ለህ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እርስዋም ራስዋን ትላጫለች፥ ጥፍርዋንም ትቈርጣለች፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 21:12
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የነጻውም ሰው ልብሱን ያጥባል፥ ጠጉሩንም ሁሉ ይላጫል፥ በውኃም ይታጠባል፥ ንጹሕም ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈር ይገባል፥ ነገር ግን ከድንኳኑ በውጭ ሆኖ ሰባት ቀን ይቀመጣል።


በሰባተኛውም ቀን ጠጉሩን ሁሉ ይላጫል፤ ራሱንም፥ ጢሙንም፥ ቅንድቡንም፥ የገላውንም ጠጉር ሁሉ ይላጫል፤ ከዚያም ልብሱን ያጥባል፥ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፤ እርሱም ንጹሕ ይሆናል።


“ሰውም በአጠገቡ ድንገት ቢሞት እርሱም የተቀደሰውን ራሱን ቢያረክስ፥ እርሱ በሚነጻበት ቀን ራሱን ይላጫል፤ በሰባተኛው ቀን ይላጨዋል።


ራስዋን ሳትሸፍን ግን የምትጸልይ ወይም ትንቢት የምትናገር ሴት ሁሉ ራስዋን ታዋርዳለች፤ እንደ ተላጨች ያህል ትቆጠራለችና።


ሴትም ራስዋን የማትከናነብ ከሆነ ደግሞ ጠጉርዋን ትቆረጥ፤ ለሴት ግን ጠጉርዋን መቆረጥ ወይም መላጨት የሚያሳፍር ከሆነ ራስዋን ትሸፍን።


ስለ ቀድሞ አኗኗሯችሁም፥ በሚያታልል ምኞቱ የጎደፈውንና የተበላሸውን፥ አሮጌ ሰው አውልቃችሁ እንድትጥሉ ተምራችኋል፤


ከምርኮኞቹ መካከል መልከ መልካም ሴት አይተህ ብትማርክህ፥ ሚስትህ ልታደርጋት ትችላለህ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች