ዘዳግም 20:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 “አንድን ከተማ ተዋግተህ ለመያዝ የረጅም ጊዜ ከበባ ካደረግህ፥ ዛፎቹን በመጥረቢያ ጨፍጭፈህ አታጥፋ፤ የእነርሱን ፍሬ መብላት ትችላለህና አትቁረጣቸው፤ ከበህ የምታጠፋቸው የሜዳ ዛፎች ሰዎች ናቸውን? ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 አንድን ከተማ ተዋግተህ ለመያዝ የረጅም ጊዜ ከበባ ካደረግህ፣ ዛፎቹን በመጥረቢያ ጨፍጭፈህ አታጥፋ፤ የእነርሱን ፍሬ መብላት ትችላለህና አትቍረጣቸው፤ ከብበህ የምታጠፋቸው የሜዳ ዛፎች ሰዎች ናቸውን? ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 “አንዲት ከተማ ለመማረክ በምትዘጋጅበት ጊዜ ከበባው ረጅም ጊዜ የወሰደ እንደ ሆነ የዛፎቹ ፍሬ ምግብ ሊሆኑህ ስለሚችሉና ዛፎችም እንደ ሰዎች ከበባ የሚደረግባቸው ስላልሆኑ ዛፎችን አትቊረጥ። የሜዳ ዛፎችን ከበባ የምታደርግባቸው ሰዎች ናቸውን? ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 “ከተማዪቱን ለመውጋትና ለመውሰድ ብዙ ቀን ብትከብባት፥ ምሳርህን አንሥተህ ዛፎችዋን አትቍረጥ፤ ከእነርሱ ትበላለህና አትቍረጣቸው፤ ወደ አንተ ይመጣና ወደ ቅጥርህም ይገባ ዘንድ የምድር ዛፍ ሰው መሆኑ ነውን? ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 ከተማይቱን ለመውሰድ በመውጋት ብዙ ቀን ከብበህ ባስጨነቅሃት ጊዜ፥ ምሳርህን አንሥተህ ዛፎችዋን አትቁረጥ፤ ከእነርሱ ትበላለህና አትቁረጣቸው፤ ከብበህ የምታጠፋው የምድር ዛፍ ሰው መሆኑ ነውን? ምዕራፉን ተመልከት |