Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 2:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 በዚያን ጊዜም ከተሞቹን ሁሉ ወሰድን የተቀመጡባቸውንም ወንዶች፥ ሴቶች፥ ሕፃናቶችንም ሁሉን አጠፋን፥ አንዳችም አላስቀረንም፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 በዚያ ጊዜ ከተሞቹን በሙሉ ወስደን የሚኖሩባቸውን ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆቻቸውን ጭምር ፈጽመን አጠፋናቸው፤ አንዳቸውንም በሕይወት አላስቀረንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ወዲያውም እያንዳንዱን ከተማ ወረን አቃጠልነው፤ በነዚያ ከተሞች የነበሩትንም ሰዎች ወንዶችንና ሴቶችን፥ ሕፃናትንም ጭምር አንድ እንኳ በሕይወት ሳናስቀር ሁሉንም ደመሰስን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 በዚ​ያን ጊዜም ከተ​ሞ​ቹን ሁሉ ወሰ​ድን፤ ከተ​ማ​ው​ንም ሁሉ፥ ሴቶ​ች​ንም፥ ሕፃ​ኖ​ች​ንም አጠ​ፋን፤ አን​ዳ​ችም የሸሸ በሕ​ይ​ወት አላ​ስ​ቀ​ረ​ንም፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 በዚያን ጊዜም ከተሞቹን ሁሉ ወሰድን የተቀመጡባቸውንም ሰዎች ሁሉ ሴቶችንም ሕፃናቶችንም አጠፋን፤ አንዳችም አላስቀረንም፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 2:34
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አሁንም ሂድ፤ አማሌቃውያንን ውጋ፤ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፤ አንዱንም አታስቀር፤ ወንዱንም ሴቱንም፥ ልጁንም ሕፃኑንም፥ የቀንድ ከብቱንም በጉንም፥ ግመሉንም አህያውንም ግደል።’ ”


ጌታ አምላክህም በእጅህ አሳልፎ በሰጣቸውና ድል በምትነሣበት ጊዜ፥ ፈጽመህ አጥፋቸው፥ ከእነርሱም ጋር ቃል ኪዳን አታድርግ፥ አትማራቸውም፥


በሐሴቦንም ንጉሥ በሴዎን እንዳደረግን ፈጽሞ ደመሰስናቸው፥ እያንዳንዱን ከተማ፥ ወንዶችን፥ ሴቶችና ሕፃናት ሁሉ አጠፋናቸው።


የእስራኤልም ልጆች የእነዚህን ከተሞች ምርኮ ሁሉ ከብቶቹንም ለራሳቸው ዘረፉ፤ ሰዎቹን ሁሉ ግን እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍ ስለት መቱአቸው፥ እስትንፋስ ያለውንም ሁሉ አላስቀሩም።


እስራኤል ኃጢአት ሠርቶአል፤ ያዘዝኋቸውንም ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋል፤ እርም የሆነውንም ነገር ወሰዱ፥ ሰረቁም፥ ዋሹም፥ በዕቃቸውም ውስጥ ሸሸጉት።


እንደ እርሱም ለጥፋት የምትሆን እንዳትሆን ርኩስን ነገር ወደ ቤትህ አታግባ፤ ርጉም ነውና ተጸየፈው፥ ጥላውም።


መልሰውም ኢያሱን እንዲህ አሉት፦ “እኛ ባርያዎችህ ምድሪቱን ሁሉ እንዲሰጣችሁ፥ በእርሷም የሚኖሩትን ሁሉ ከፊታችሁ እንዲያጠፋ ጌታ አምላክህ ባርያውን ሙሴን እንዳዘዘ በእውነት ሰምተናል፥ ስለዚህም ከእናንተ የተነሣ ስለ ነፍሳችን እጅግ ስለ ፈራን ይህን ነገር አድርገናል።


በከተማይቱም የነበሩትን ሁሉ፥ ወንዱንና ሴቱን፥ ሕፃኑንና ሽማግሌውን፥ በሬውንም በጉንም አህያውንም፥ በሰይፍ ስለት ፈጽመው አጠፉ።


በዚያም ቀን ኢያሱ መቄዳን ያዛት፥ እርሷንና ንጉሥዋንም በሰይፍ ስለት መታ፤ በእርሷም ያሉትን ሰዎች ሁሉ ፈጽሞ አጠፋቸው፥ ከእነርሱም አንድም እንኳ አላስቀረም፤ በኢያሪኮም ንጉሥ ላይ እንዳደረገው እንዲሁ በመቄዳ ንጉሥ ላይ አደረገ።


እንዲሁም ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ ተራራማውን አገር ደቡቡንም ቈላውንም የተዳፋቱንም ስፍራ ነገሥታቶቻቸውንም ሁሉ መታ፤ ማንንም አላስቀረም፤ የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዳዘዘውም እስትንፋስ ያለውንም ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች