ዘዳግም 2:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)31 “ጌታም፦ ‘ሴዎንንና ምድሩን በእጅህ አሳልፌ መስጠት፥ እነሆ፥ ጀመርሁ፤ ምድሩን ትገዛት ዘንድ መውረስ ጀምር’ አለኝ።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም31 እግዚአብሔርም፣ “እነሆ፤ ሴዎንንና አገሩን ለእናንተ አሳልፌ ልሰጣችሁ ተነሥቻለሁ፤ አሁንም እርሱን አሸንፋችሁ ምድሩን ለመውረስ ተነሡ” አለኝ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም31 “ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ ‘ተመልከት እኔ ንጉሥ ሲሖንንና ምድሩን በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ፤ አሁን ድል በማድረግ ምድሩን ወርሰህ ስፈርበት።’ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)31 እግዚአብሔርም፦ ‘የሐሴቦንን ንጉሥ አሞራዊውን ሴዎንንና ምድሩን በፊትህ በእጅህ አሳልፌ መስጠት እነሆ፥ ጀመርሁ፤ ምድሩን ትገዛ ዘንድ መውረስ ጀምር’ አለኝ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)31 እግዚአብሔርም፦ ሴዎንንና ምድሩን በእጅህ አሳልፌ መስጠት፥ እነሆ፥ ጀመርሁ፤ ምድሩን ትገዛት ዘንድ መውረስ ጀምር አለኝ። ምዕራፉን ተመልከት |