Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 19:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 “አምላክህ ጌታ እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር ውስጥ ለአንተ በሚተላለፍልህ ርስት ላይ የቀድሞ ሰዎች ያስቀመጡትን የባልጀራህን የድንበር ምልክት አታንሣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 አምላክህ እግዚአብሔር እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር ውስጥ ለአንተ በሚተላለፍልህ ርስት ላይ የቀድሞ ሰዎች ያስቀመጡትን የባልንጀራህን የድንበር ምልክት አታንሣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 “እግዚአብሔር አምላክህ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ለአንተ በተሰጠው ድርሻና በጐረቤትህ መካከል በቀድሞ ትውልድ የተተከለውን የድንበር ምልክት አታፍርስ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 “አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳት ዘንድ በሚ​ሰ​ጥህ ምድር፤ በም​ት​ካ​ፈ​ላት ርስ​ትህ አባ​ቶ​ችህ የተ​ከ​ሉ​ትን የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህን የድ​ን​በር ምል​ክት አት​ን​ቀል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 አምላክህ እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ በሚሰጥህ ምድር በምትወርሳት ርስትህ የቀደሙ ሰዎች የተከሉትን የባልንጀራህን የድንበር ምልክት አትንቀል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 19:14
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አባቶችህ የሠሩትን የቀድሞውን የድንበር ምልክት አታፋልስ።


“‘የባልንጀራውን የድንበር ምልክት ከቦታው የሚያንቀሳቅስ የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።


የይሁዳ አለቆች ድምበርን እንደሚያፈርሱ ሰዎች ሆነዋል፤ እኔም መዓቴን እንደ ውኃ በእነርሱ ላይ አወርድባቸዋለሁ።


የቀድሞውን የድንበር ምልክት አታፍልስ፥ ወደ ድሀ አደጎች እርሻ አትግባ፥


የድንበሩን ምልክት የሚያፈርሱ አሉ፥ መንጋዎቹን ቀምተው ያሰማራሉ።


ጌታ የትዕቢተኞችን ቤት ይነቅላል፥ የባልቴትን ዳርቻ ግን ያጸናል።


ሳይሸምቅበት፥ ነገር ግን እግዚአብሔር ድንገት በእጁ ቢጥለው፥ የሚሸሽበት ስፍራ እኔ አዘጋጅልሃለሁ።


በዚያም ጊዜ እንዲህ ብዬ አዘዝኋችሁ፦ “ጌታ አምላካችሁ ይህችን ምድር ርስት አድርጎ ሰጥቶአችኋል፤ የእናንተ ጦር ሰዎች ሁሉ ታጥቀው በወንድሞቻችሁ በእስራኤል ልጆች ፊት ትሻገራላችሁ።


ከዚህ በኋላ ሙሴ ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ በስተ ምሥራቅ ሦስት ከተሞች በመለየት ከለለ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች