Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 17:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 “በአምላክህ በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ነውና፥ ከበሬ ወይም ከበግ ነውር ወይም ጉድለት ያለበትን ለአምላክህ ለጌታ አትሠዋ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እንከን ወይም ጕድለት ያለበትን በሬ ወይም በግ በርሱ ዘንድ አስጸያፊ ነውና ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አትሠዋ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 “ከከብት ወይም ከበግ መንጋዎች መካከል አንዳች ነውር ያለበትን እንስሳ ለእግዚአብሔር ለአምላክህ መሥዋዕት አድርገህ አታቅርብ፤ ይህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 “በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ጠላ ነውና ነውር ወይም ክፉ ነገር ያለ​በ​ትን በሬ ወይም በግ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አት​ሠዋ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነውና ነውር ወይም ክፉ ነገር ያለበትን በሬ ወይም በግ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አትሠዋ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 17:1
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንድ እንስሳ እንከን ያለው፥ አንካሳ ወይም ዕውር፥ ወይም ደግሞ ማናቸውም ዓይነት ከባድ ጉድለት ያለበት ከሆነ ለጌታ ለእግዚአብሔር አትሠዋው፤


“የታወረውን ለመሥዋዕት ስታቀርቡ፥ ይህ ክፉ አይደለምን? አንካሳውንና የታመመውን ስታቀርቡ ይህ ክፉ አይደለምን? ይህንን ለገዢህ አቅርብ፤ በውኑ በአንተ ደስ ይለዋልን? ወይስ ፊትህንስ ይቀበላልን?” ይላል የሠራዊት ጌታ።


ስለ ተሳልኸው ስእለት ሁሉ የአመንዝራይቱን ዋጋና የውሻውን ዋጋ ወደ አምላክህ ወደ ጌታ ቤት አታቅርብ፥ ሁለቱም በጌታ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያጸይፉ ናቸውና።


ከዚያ በኋላ የፈታት የመጀመሪያ ባሏ፥ የረከሰች በመሆኗ እንደገና መልሶ ሊያገባት አይችልም፤ ይህ በጌታ ፊት አስጸያፊ ነው። ጌታ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ላይ ኃጢአት አታምጣ።


ነገር ግን ነውርና እድፍ እንደሌለው በግ ደም፥ በክርስቶስ ክቡር ደም ነው፥


ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበው የክርስቶስ ደም እንዴት ልቆ፥ ሕያው እግዚአብሔርን ለማምለክ፥ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን!


የኀጥኣን መሥዋዕት በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ የቅኖች ጸሎት ግን በእርሱ ዘንድ የተወደደ ነው።


የሐሰት ሚዛን በጌታ ፊት አስጸያፊ ነው፥ እውነተኛ ሚዛን ግን ደስ ያሰኘዋል።


ጌታ የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባተኛውንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፋቸዋለች፥


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ያሉትን ነገሮች የሚፈጽመውንና የሚያምታታውን ሁሉ ይጸየፈዋልና።


የእናንተ ጠቦት ነውር የሌለበት፥ ተባዕት፥ የአንድ ዓመት ይሁን፤ ከበጎች ወይም ከፍየሎች ውሰድ።


ከእነርሱም በኋላ፥ ዐቅመ ደካማ፥ መልካቸው እጅግ የከፋና ዐጥንታቸው የወጣ ሌሎች ሰባት ላሞች ወጡ፤ እነዚያን የመሰሉ የሚያስከፋ መልክ ያላቸው ላሞች በግብጽ ምድር ከቶ አይቼ አላውቅም።


ሁለት ዓይነት ሚዛንና ሁለት ዓይነት መስፈሪያ፥ ሁለቱ በጌታ ፊት ርኩሳን ናቸው።


“መባውም የሚቃጠል መሥዋዕት ከበሬ መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፤ በጌታ ፊት እንዲሠምርለት በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል።


ለጌታም መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ አንድ ወይፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ታቀርባላችሁ፤ ነውር የሌለባቸውም ይሁኑ።


የተቀረጸውንም የአምላኮቻቸውን ምስል በእሳት ታቃጥላለህ፤ በእነርሱ ላይ የተለበጠውን ብር ወይም ወርቅ አትመኝ፥ በጌታ አምላካችሁም ዘንድ ርኩስ ነውና እንዳትጠመድበት ከእርሱ ምንም አትውሰድ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች