ዘዳግም 16:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 አምላክህ ጌታ በፍሬህ ሁሉ በእጅህም ሥራ ሁሉ ይባርክሃልና ጌታ በመረጠው ስፍራ ለአምላክህ ለጌታ ሰባት ቀን በዓል ታደርጋለህ፥ አንተም ፈጽሞ ደስ ይልሃል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በዓሉን ሰባት ቀን አክብር፤ አምላክህ እግዚአብሔር በእህል ምርትህና በእጅህ ሥራ ሁሉ ይባርክሃል፤ ደስታህም ፍጹም ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 አምላክህ እግዚአብሔር በሚመርጠው ቦታ ለሰባት ቀን ለእርሱ በዓል ታደርጋለህ፤ እግዚአብሔር አምላክህ፥ በምርትህና በምታደርጋቸው ድርጊቶች ሁሉ ስለሚባርክህ በዓሉን በደስታ ታከብራለህ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 አምላክህ እግዚአብሔር ለራሱ በመረጠው ስፍራ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ሰባት ቀን በዓል ታደርጋለህ፤ አምላክህ እግዚአብሔር በፍሬህ ሁሉ፥ በእጅህም ሥራ ሁሉ ይባርክሃልና። አንተም ፈጽሞ ደስ ይልሃልና። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 አምላክህ እግዚአብሔር በፍሬህ ሁሉ በእጅህም ሥራ ሁሉ ይባርክሃልና እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ሰባት ቀን በዓል ታደርጋለህ፤ አንተም ፈጽሞ ደስ ይልሃል። ምዕራፉን ተመልከት |