Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 14:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 “ርኩስ የሆነውን ማንኛውንም ነገር አትብሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ማንኛውንም ርኩስ ነገር አትብላ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 “ርኩስ የሆነውን ማንኛውንም ነገር አትብሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 “ርኩ​ስን ነገር ሁሉ አት​ብሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3-4 ርኩስን ነገር ሁሉ አትብላ። የምትበሉአቸው እንስሶች እነዚህ ናቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 14:3
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኔም እንዲህ አልሁ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወይኔ! እነሆ፥ ሰውነቴ አልረከሰችም፥ ከልጅነቴ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ፥ የሞተ ወይም እንስሳ የገደለውን ከቶ አልበላሁም፥ ርኩስም ሥጋ በአፌ ውስጥ አልገባም።


በራሱ ርኩስ የሆነ ነገር እንደሌለ በጌታ በኢየሱስ ሆኜ አውቄአለሁ፤ ተረድቼአለሁም፤ ነገር ግን ምንም ርኩስ እንዲሆን ለሚቆጥር ለእርሱ ርኩስ ነው።


ስለዚህ ንጹሑን እንስሳ ከርኩሱ፥ ንጹሑንም ወፍ ርኩስ ከሆነው ትለያላችሁ፤ ለእናንተ ርኩሶች ናቸው ብዬ በለየኋቸው በእንስሳና በወፍ በምድርም ላይ በሚርመሰመሱ ነፍሳት ሁሉ ራሳችሁን አታርክሱ።


በሚርመሰመሱ ተንቀሳቃሾች ሁሉ የገዛ አካላችሁን አታጸይፉ፤ እንዳትረክሱም የገዛ አካላችሁን በእነርሱ አታርክሱ።


ለንጹሖች ሁሉ ነገር ንጹሕ ነው፤ ለርኩሳንና ለማያምኑ ግን ንጹሕ የሆነ ነገር ምንም የለም፤ ነገር ግን አእምሮአቸውም ሆነ ኅሊናቸው ረክሶአል።


ማንም ግን “ይህ ለጣዖት የተሠዋ ነው፤” ቢላችሁ ይህን በነገራችሁ ሰው ምክንያትና በኅሊናም ምክንያት ሥጋውን አትብሉ፤


በመቃብርም መካከል የሚቀመጡ፥ ምሽቱንም በስውርም ስፍራ የሚያሳልፉ፥ የእሪያ ሥጋም የሚበሉ ናቸው። ማሰሮዎቻቸው በረከሰ ነገር የተሞሉ ናቸው።


ከንጹሕ እንስሳ ሁሉ ሰባት ሰባት ተባዕትና እንስት፥ ንጹሕ ካልሆነ እንስሳም ሁለት ሁለት ተባዕትና እንስት፤


“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብላችሁ ተናገሩ፦ በሕይወት ከሚኖሩ ከምድር እንስሶች ሁሉ የምትበሉአቸው እነዚህ ናቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች