ዘዳግም 12:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 የሚቃጠል መሥዋዕትህን፥ ሥጋውንም ደሙንም በጌታ አምላክህ መሠዊያ ላይ አቅርብ። የመሥዋዕትህ ደም በጌታ አምላክህ መሠዊያ ላይ ይፍሰስ፤ ሥጋውን ግን መብላት ትችላለህ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም27 የሚቃጠል መሥዋዕትህን፣ ሥጋውንም ደሙንም በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ አቅርብ። የመሥዋዕትህ ደም በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ይፍሰስ፤ ሥጋውን ግን መብላት ትችላለህ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም27 የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን፥ ማለትም ሥጋውንና ደሙን ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ አቅርብ። የሌሎች መሥዋዕቶችህ ደም ከአምላክህ ከእግዚአብሔር መሠዊያ አጠገብ ይፍሰስ፤ ሥጋውን ግን ልትበላ ትችላለህ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 ሥጋውን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገህ፥ በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ አቅርብ፤ የመሥዋዕትህም ደም በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ይፍሰስ፥ ሥጋውንም ብላው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)27 የሚቃጠለውንም መሥዋዕትህን፥ ሥጋውንና ደሙን፥ በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ አቅርብ፤ የመሥዋዕትህም ደም በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ይፍሰስ፥ ሥጋውንም ብላው። ምዕራፉን ተመልከት |