ዘዳግም 12:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 “ሆኖም ጌታ አምላክህ በሚሰጥህ መጠን፥ በየትኛውም ከተማህ፥ እንስሳትህን ሚዳቋም ሆነ ድኩላ ዐርደህ የምትፈልገውን ያህል ሥጋ ብላ። በሥርዓቱ መሠረት ንጹሕ የሆነም ሆነ ያልሆነ ሰው ከዚሁ ሥጋ ሊበላ ይችላል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ሆኖም ከአምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ በረከት፣ በየትኛውም ከተማህ፣ እንስሳትህን ሚዳቋም ሆነ ድኵላ ዐርደህ የምትፈልገውን ያህል ሥጋ ብላ፤ በሥርዐቱ መሠረት ንጹሕ የሆነም ሆነ ያልሆነ ሰው ከዚሁ ሥጋ ሊበላ ይችላል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 “ሆኖም በሚያሰኛችሁ ጊዜ ሁሉ እግዚአብሔር አምላካችሁ በሰጣችሁ በረከት መሠረት ከከተሞቻችሁ በማናቸውም ቦታ ዐርዳችሁ ልትበሉ ትችላላችሁ፤ የአጋዘንና የሚዳቋ ሥጋ ለመብላት እንደሚችል ንጹሕ የሆነ ወይም ንጹሕ ያልሆነ ሰው ያን የታረደውን ሥጋ ሊበላው ይችላል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 “ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ሰጠህ በረከት፥ እንደ ፈቀድህ፥ በሀገርህ ሁሉ ውስጥ አርደህ ሥጋን ብላ፤ ከአንተ ንጹሕ ሰው፥ ንጹሕም ያልሆነ ሰው እንደ ሚዳቋና እንደ ዋላ ያለውን ይብላው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ሰጠህ በረከት፥ ሰውነትህ እንደ ፈቀደ፥ በደጆችህ ሁሉ ውስጥ አርደህ ብላ፤ ንጹሕ ሰው ንጹሕም ያልሆነ ሰው እንደ ሚዳቍና እንደ ዋላ ያለውን ይብላው። ምዕራፉን ተመልከት |