Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 11:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 “አምላካችሁን ጌታን ትወዱ ዘንድ፥ በመንገዶቹም ሁሉ ትሄዱና ከእርሱም ጋር ትጣበቁ ዘንድ እንድትከተሏቸው የምሰጣችሁን እነዚህን ትእዛዞች ሁሉ በጥንቃቄ ብትጠብቁ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትወድዱ ዘንድ፣ በመንገዶቹም ሁሉ ትሄዱና ከርሱም ጋራ ትጣበቁ ዘንድ እንድትከተሏቸው የምሰጣችሁን እነዚህን ትእዛዞች ሁሉ በጥንቃቄ ብትጠብቁ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 “ስለዚህም እኔ የሰጠኋችሁን ትእዛዞች በጥንቃቄ ፈጽሙ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁን ውደዱ፤ በእርሱ መንገድም በመጓዝ ለእርሱ ታማኞች ሁኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትወ​ድዱ ዘንድ፥ በመ​ን​ገ​ዱም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ እር​ሱ​ንም ትከ​ተሉ ዘንድ፥ ዛሬ ለእ​ና​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛዝ ሁሉ ብት​ጠ​ብቁ ብታ​ደ​ር​ጉ​አ​ትም፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትወድዱ ዘንድ፥ በመንገዱም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ ከእርሱም ጋር ትጣበቁ ዘንድ፥ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዝ ሁሉ ብትጠብቁ ብታደርጉአትም፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 11:22
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ጌታ አምላክህን በመውደድ ዛሬ እኔ የምሰጣችሁን ትእዛዞች በታማኝነት ብትጠብቁ፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹም ነፍሳችሁም እርሱን በማገልገል፥ በታማኝነት ብትጠብቁ፥


ለእናንተ ያዘዘውን የጌታ የአምላካችሁን ምስክሩን፥ ሥርዓቱንም፥ ትእዛዛቱንም አጥብቃችሁ ያዙ።


ጌታ እግዚአብሔርን ፍራ፥ እርሱንም አምልክ፥ ከእርሱም አትነጠል፥ በስሙም ማል።


ከእንግዲህም ወዲህ ጻድቅ ፈራጅ የሆነ ጌታ በዚያ ቀን ሊሸልመኝ የጽድቅ አክሊል አዘጋጅቶ ይጠብቀኛል፤ ደግሞም ለእኔ ብቻ ሳይሆን መገለጡን በፍቅር ለናፈቁት ሁሉ ነው።


እርሱም መጥቶ የእግዚአብሔርን ጸጋ ባየ ጊዜ ደስ አለው፤ ሁሉንም በልባቸው ፈቃድ በጌታ ጸንተው ይኖሩ ዘንድ መከራቸው፤


እርሱም እንዲህ አለው “‘ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፥ በፍጹም ነፍስህ፥ በፍጹም ሐሳብህ ውደድ።’


ጌታ አምላክህን ውደደው፤ ለቃሉም ታዘዝ፤ ከእርሱም ጋር ተጣበቅ። ጌታ ለአባቶችህም ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ሊሰጣቸው በማለላቸው ምድር የዕድሜህም ዘመን ሕይወትም ማለት ነው።”


ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ትቶ ከሚስቱ ጋር ይተባበራል፤ ሁለቱም አንድ አካል ይሆናሉ።


“እንግዲህ ጌታ አምላክህን ውደድ፤ ግዴታውን፥ ሥርዓቱን፥ ሕጉንና ትእዛዙን ሁልጊዜ ጠብቅ።


አቤቱ፥ ሕግህን ተጠጋሁ፥ አታሳፍረኝ።


ጌታን እግዚአብሔርን እንድትወድና ምንጊዜም በመንገዱ እንድትሄድ ዛሬ የማዝህን እነዚህን ሕግጋት ሁሉ በጥንቃቄ እምትጠብቅ ከሆነ፥ በእነዚህ ላይ ሌሎች ሦስት ከተሞችን ትጨምራለህ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች