Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 10:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ብቻ ጌታ ስለ አባቶችህ ደስ ብሎታል፥ እነርሱንም ወድዶአል፥ ከእነርሱም በኋላ እናንተን ዘራቸውን እንደ ዛሬው ሁሉ ከአሕዛብ ሁሉ መካከል መረጠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ነገር ግን እግዚአብሔር አባቶችህን ስላፈቀረ፣ ወደዳቸው፤ ዛሬም እንደ ሆነው የእነርሱ ዘር የሆናችሁትን እናንተን ከአሕዛብ ሁሉ ለይቶ መረጣችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶችህ የነበረው ፍቅር እጅግ ብርቱ ከመሆኑ የተነሣ፥ ዛሬም አንተን ከብዙ አሕዛብ መካከል መርጦአል፤ አንተም እስከ አሁን የእርሱ ምርጥ ሕዝብ ነህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁን መረ​ጣ​ቸው፤ ወደ​ዳ​ቸ​ውም፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ እና​ን​ተን ዘራ​ቸ​ውን እንደ ዛሬው ሁሉ ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ መረጠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ብቻ እግዚአብሔር ስለ አባቶችህ ደስ ብሎታል፥ እነርሱንም ወድዶአል፤ ከእነርሱም በኋላ እናንተን ዘራቸውን እንደ ዛሬው ሁሉ ከአሕዛብ ሁሉ መካከል መረጠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 10:15
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ባርያዎቹ የሆናችሁ የእስራኤል ዘር ሆይ! ለእርሱም የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ!


ጌታ ያዕቆብን ለራሱ፥ እስራኤልንም ግዛቱ አድርጎ መርጦታልና፥


እጅህ አሕዛብን አባረረች፥ እነርሱንም ተከልህ፥ አሕዛብን አስጨንቀህ እነሱን አለመለምክ።


እንዲህም ይላል፦ “እኔ ከምድር ወገኖች ሁሉ እናንተን ብቻ አውቄአችኋለሁ፤ ስለዚህ ስለ ኃጢአታችሁ ሁሉ እበቀላችኋለሁ።


ጌታስ በእኛ ደስ የሚሰኝ ቢሆን ወተትና ማር ወደምታፈስሰው ወደዚች ምድር ያገባናል እርሷንም ይሰጠናል።


በወንጌልስ በኩል በእናንተ ምክንያት ጠላቶች ናቸው፤ በምርጫ በኩል ግን በአባቶች ምክንያት ተወዳጆች ናቸው፤


አባቶቻችሁን ወድዶአልና ከእነርሱ በኋላ ዘራቸውን መረጠ፥ ከእናንተ ጋር ሆኖ በታላቅ ኃይሉ ከግብጽ አወጣችሁ።


እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችሁ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች