ቈላስይስ 4:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 የታሰርኩበት ምክንያት የሆነውን የክርስቶስን ምሥጢር ለማወጅ እግዚአብሔር ለቃሉ በር እንዲከፍትልን ስለ እኛ ደግሞ ጸልዩ፤ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 እኔ እስረኛ የሆንሁለትን የክርስቶስን ምስጢር ማወጅ እንድንችል፣ እግዚአብሔር የቃሉን በር እንዲከፍትልን ስለ እኛ ደግሞ ጸልዩ፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 ከዚህም ጋር እግዚአብሔር ለቃሉ በር እንዲከፍትልንና እኔ በእርሱ ምክንያት ታስሬ የምገኝበትን የክርስቶስን ምሥጢር ማብሠር እንድንችል ለእኛም ጸልዩ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 ስለ እርሱ የታሰርሁለትን የእግዚአብሔርን ምሥጢር እንድንናገር፥ እግዚአብሔር የቃሉን በር ይከፍትልን ዘንድ ለእኛም ደግሞ ጸልዩልን፤ ለምኑልንም፤ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 በዚያን ጊዜም ስለ እርሱ ደግሞ የታሰርሁበትን የክርስቶስን ምሥጢር እንድንነግር እግዚአብሔር የቃሉን ደጅ ይከፍትልን ዘንድ ስለ እኛ ደግሞ ጸልዩ፤ ምዕራፉን ተመልከት |