Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ቈላስይስ 4:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ኢዮስጦስም የተባለ ኢያሱ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል፤ ከተገረዙትም ወገን የሆኑ፥ በእግዚአብሔር መንግሥት ከእኔ ጋር አብረው የሚሠሩት እነዚህ ብቻ ናቸው፤ እኔንም አጽናንተውኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ኢዮስጦስ የተባለው ኢያሱም ሰላምታ ያቀርብላችኋል። ከተገረዙት መካከል ለእግዚአብሔር መንግሥት ዐብረውኝ የሚሠሩት፣ እኔንም ያጽናኑኝ እነዚህ ብቻ ናቸው፤ እነርሱም አጽናንተውናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ኢዮስጦስ ተብሎም የሚጠራው ኢያሱ ሰላምታ ያቀርብላችኋል። ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ከእኔ ጋር አብረው ከሚሠሩት ሰዎች መካከል የአይሁድ ወገኖች የሆኑት እነዚህ ብቻ ናቸው፤ እኔንም አጽናንተውኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ኢዮ​ስ​ጦስ የተ​ባለ ኢያ​ሱም፥ ከግ​ዙ​ራን ሰዎች ወገን የሚ​ሆኑ እነ​ዚህ ሰላም ይሏ​ች​ኋል። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ሥራ ረዳ​ቶች እነ​ዚህ ብቻ ናቸው፤ እነ​ር​ሱም እኔን አጽ​ና​ን​ተ​ው​ኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ቈላስይስ 4:11
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከጴጥሮስም ጋር የመጡት ሁሉ ከተገረዙት ወገን የሆኑ ምዕመናን በአሕዛብ ላይ ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ስለ ፈሰሰ ተገረሙ፤


ጴጥሮስም ወደ ኢየሩሳሌም በወጣ ጊዜ ከተገረዙት ወገን የሆኑት ሰዎች ከእርሱ ጋር ተከራክረው


በክርስቶስ ኢየሱስ አብረውኝ ለሚሠሩ ለፕሪስካና ለአኪላ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤


ለተገረዙትም አባት ነው፤ ለተገረዙት ብቻ ሳይሆን፥ ነገር ግን አባታችን አብርሃም ከመገረዙ በፊት የነበረውን የእምነቱን ፈለግ ለሚከተሉ ጭምር ነው።


እንግዲህ፥ ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ እንደ መሆናችን፥ የእግዚአብሔርን ጸጋ በከንቱ እንዳትቀበሉ እንለምናለን፤


ስለዚህ እናንተ አስቀድሞ በትውልድ አሕዛብ የነበራችሁ፥ በአካል ላይ በሰው እጅ ከተደረገው የተነሣ፥ “ተገርዘናል” በሚሉት፥ “ያልተገረዛችሁ” የተባላችሁትን ያን አስታውሱ፤


አንተም ደግሞ በሥራዬ አብረህ የተጠመድህ እውነተኛ ሆይ! ከእኔ ጎን በመቆም ከቀለሜንጦስ ጋር አብረው በወንጌል ሥራ ተጋድለዋልና እነዚህን ሴቶችና የተቀሩትን በሕይወት መጽሐፍ የተጻፉትን ከእኔ ጋር አብረው የሚሠሩትን እንድትረዱአቸው እለምንሃለሁ።


የተወደደ ወንድምና የታመነ አገልጋይ በጌታም አብሮኝ ባርያ የሆነ ቲኪቆስ እኔ ስላለሁበት ሁኔታ ሁሉ ይነግራችኋል፤


ስለ እምነታችሁም እንዲያጸናችሁና እንዲመክራችሁ ወንድማችንን፥ የእግዚአብሔርንም አገልጋይ ከእኛ ጋርም አብሮ በክርስቶስ ወንጌል የሚሠራውን ጢሞቴዎስን ላክነው፤


ስለዚህ ወንድሞች ሆይ! በእምነታችሁ በኩል በችግራችንና በመከራችን ሁሉ ስለ እናንተ ተጽናናን፤


የማይታዘዙና ከንቱ ነገርን የሚያወሩ የሚያታልሉ በተለይም ከተገረዙት ወገን የሆኑ ብዙ ሰዎች አሉና፤


ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ እስረኛ ከሆነው ጳውሎስና ከወንድሙ ጢሞቴዎስ፥ ለተወደደውና አብሮን ለሚሠራ ለፊልሞና፥


አብረውኝም የሚሠሩ ማርቆስና አርስጥሮኮስ ዴማስም ሉቃስም ሰላምታ ያቀርቡልሃል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች