Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ቈላስይስ 3:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 የሚበድልም እንደ በደሉ መጠን ብድራቱን ይቀበላል፤ ለሰው ፊትም አድልዎ የለምና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 በደለኛውም የእጁን ያገኛል፤ አድልዎም የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 በእግዚአብሔር ዘንድ አድልዎ ስለሌለ ክፉ የሚሠራም ስለ ክፉ ሥራው ቅጣቱን ይቀበላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 የሚ​በ​ድል ግን ፍዳ​ውን ያገ​ኛል፤ እር​ሱም አያ​ደ​ላ​ለ​ትም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 የሚበድልም የበደለውን በብድራት ይቀበላል፥ ለሰው ፊትም አድልዎ የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ቈላስይስ 3:25
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጴጥሮስም አፉን ከፍቶ እንዲህ አለ “እግዚአብሔር ለሰው ፊት እንዳያደላ ነገር ግን በአሕዛብ ሁሉ እርሱን የሚፈራና ጽድቅን የሚያደርግ በእርሱ የተወደደ እንደሆነ በእውነት አስተዋልሁ።


በእግዚአብሔር ዘንድ ማዳላት የለምና።


መልካም ሆነ ወይም ክፉ፥ በሥጋችን እንደ ሠራነው ዋጋችንን ለመቀበል፥ ሁላችን በክርስቶስ የፍርድ ዙፋን ፊት እንቆማለን።


አስቀድመን ደግሞ እንደ ነገርናችሁና እንደ መሰከርንላችሁ፥ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና፥ ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ፤ ወንድሙንም አያታልል።


ምክንያቱም ጌታ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ፥ የጌቶችም ጌታ፥ ታላቅ አምላክ፥ ኃያልም፥ የሚያስፈራም፥ በፍርድ የማያደላ፥ ጉቦም የማይቀበል ነው።


ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ የምትጠሩት ከሆነ፥ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።


እናንተም ጌቶች ሆይ! ዛቻውን ትታችሁ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ በእነርሱና በእናንተ ላይ የሚገዛው ጌታ በሰማይ እንዳለ ለሰው ፊትም እንደማያዳላ ታውቃላችሁ።


እንግዲህ አሁን ጌታን መፍራት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በአምላካችንም በጌታ ዘንድ በደልና ለሰው ፊት ማድላት መማለጃም መውሰድ የለምና ሁሉንም ነገር ተጠንቅቃችሁ አድርጉ።”


በፍርድም አድልዎ አታድርጉ፥ ታላቁን እንደምትሰሙ፥ ታናሹንም እንዲሁ ስሙ፥ ፍርድ ለእግዚአብሔር ነውና ከሰው ፊት አትፍሩ፥ አንድ ነገር ቢከብዳችሁ እርሱን ወደ እኔ አምጡት፥ እኔም እሰማዋለሁ፤’


በመላእክት የተነገረው ቃል በጽናት ከተረጋገጠ፥ እያንዳንዱም መተላለፍ ወይም አለመታዘዝ ትክክለኛውን ቅጣት ከተቀበለ፥


ጌቶች ሆይ! እናንተ ደግሞ በሰማይ ጌታ እንዳላችሁ ታውቃላችሁና ባርያዎቻችሁን በጽድቅና በቅንነት ተመልከቱአቸው።


እነርሱም እንዲህ ሲሉ ጠየቁት “መምህር ሆይ! እውነትን እንደምትናገርና እንደምታስተምር በሰው ፊትም እንደማታደላ እናውቃለን፤ ይልቁንም በእውነት የእግዚአብሔርን መንገድ ታስተምራለህ፤


ስለዚህ ሰዎች ይፈሩታል፥ በልባቸውም ጠቢባን የሆኑትን ሁሉ አይመለከትም።”


እነርሱ ሁሉ የእጁ ሥራ ናቸውና ለአለቆች አያደላም፥ ሀብታሙንም ሰው ከድሀው ይበልጥ አይመለከትም።


እኛ ሁላችን መሞታችን አይቀሬ ነው፤ በመሬት ላይ እንደ ፈሰሰና ተመልሶም ሊታፈስ እንደማይችል ውሃ ነን፤ እግዚአብሔር የተሰደደ ሰው በስደት በዚያው እንዳይቀር የሚመለስበትን ሁኔታ ያመቻቻል እንጂ ሕይወቱ እንድትጠፋ አይፈቅድም።


“ፍርድን ፈጽሞ አታጓድሉ፤ ለድሀ አታድላ፥ ባለ ጠጋውንም አታክብር፤ ነገር ግን ለባልንጀራህ በጽድቅ ፍረድ።


እነዚህ የሚያጉረመርሙ፥ የሚያማርሩ፥ ክፉ ምኞታቸውን የሚከተሉ ናቸው፤ አፋቸው የትዕቢት ቃልን ይናገራል፤ለጥቅማቸው ሲሉ ሰዎችን ያደንቃሉ።


በአንዳች ነገር በድሎህ እንደሆነ ግን ወይም ብድር ያለበት እንደሆነ፥ ይህን በእኔ ላይ ቁጠር፤


የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣልና፤ በዚያን ጊዜ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ይከፍለዋል።


ባርያም ሆነ ነጻ ሰው፥ እያንዳንዱ ለሚያደርገው መልካም ነገር ሁሉ ከጌታ ብድራቱን እንደሚቀበል ታውቃላችሁ።


በእርግጥ በእግዚአብሔር ዘንድ ጽድቅ ነውና፥ መከራን የሚያደርሱባችሁን በመከራ ብድራታቸውን ይከፍላል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች