Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ቈላስይስ 3:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ሥራችሁንም ሁሉ ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉት እንዲሁ በትጋት ፈጽሙት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 የምታደርጉትን ሁሉ ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉት ቈጥራችሁ በሙሉ ልባችሁ አድርጉት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 የምታደርጉትን ሁሉ ለሰው ሳይሆን ለጌታ ኢየሱስ እንደምታደርጉት ዐይነት ከልባችሁ አድርጉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ለሰው ሳይ​ሆን ለጌታ እን​ደ​ም​ታ​ደ​ርጉ የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትን ሁሉ ከልብ አድ​ር​ጉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ፥ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ቈላስይስ 3:23
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በኢየሱስ በኩል እግዚአብሔር አብን እያመሰገናችሁ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።


በሕይወት ሆነን ብንኖር ለጌታ እንኖራለንና፤ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን። እንግዲህ በሕይወት ሆነን ብንኖር ወይም ብንሞት የጌታ ነን።


ስለ ጌታም ቤት አገልግሎት በጀመረው ሥራ ሁሉ፥ በሕጉና በትእዛዙም፥ አምላኩን ለመፈለግ በፍጹም ልቡ አደረገው፥ ተከናወነለትም።


አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና አሳብ እውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምታገኘውን ሁሉ እንደ ኃይልህ አድርግ።


በዚህ መንገድ መልካም በማድረግ የሞኞችን አላዋቂነት ዝም እንድታሰኙ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው።


ስለ ጌታ ብላችሁ ሥልጣን ለተሰጣቸው ሰዎች ሁሉ፥ ንጉሥም ቢሆን ከሁሉ በላይ እንደመሆኑ ታዘዙ።


በፍጹም ልቤ ፈለግሁህ፥ ከትእዛዝህ አታርቀኝ።


ለእውነት በመታዘዝ ነፍሳችሁን አንጽታችሁ ለወንድማማች እውነተኛ ፍቅር፥ እርስ በርሳችሁ ከልባችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።


አንድን ቀን ከሌላው የተለየ አድርጎ የሚያስብ ሰው ለጌታ ብሎ ነው፤ የሚበላም ለጌታ ብሎ ይበላል፤ እግዚአብሔርን ያመሰግናልና የማይበላም ለጌታ ብሎ አይበላም፤ እግዚአብሔርንም ያመሰግናል።


እንዳስተውል አድርገኝ፥ ሕግህንም እንድጠብቅ፥ በፍጹም ልቤም እጠብቀዋለሁ።


በዚህም ሁሉ ግን አታላይቱ ይሁዳ በሐሰት እንጂ በፍጹም ልብዋ ወደ እኔ አልተመለሰችም፥ ይላል ጌታ።


በፍጹም ልቤ ጮኽሁ፥ አቤቱ፥ ስማኝ፥ ሥርዓትህን እፈልጋለሁ።


“ስትጾሙ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ሰዎች መጾማቸውን እንዲያዩላቸው ፊታቸውን ይለውጣሉና፤ እውነት እላችኋለሁ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።


ሚስቶች ሆይ! ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤


የዳዊት መዝሙር። ነፍሴ ሆይ፥ ጌታን ባርኪ፥ አጥንቶቼም ሁሉ፥ የተቀደሰ ስሙን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች