Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ቈላስይስ 2:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እንዲሁም እግዚአብሔር በሚሰጠው ማደግ የሚያድገውን አካል ሁሉ የሚንከባከበውን በመገጣጠምያዎቹና በጅማቶቹ አብሮ የሚያስተሳስረውን ራስ በጽኑ ሳይዝ ማንም አያውግዛችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ይህ ሰው፣ አካል ሁሉ በጅማትና በማሰሪያ እየተጋጠመ ምግብንም እየተቀበለ እግዚአብሔር በሚሰጠው ማደግ ከሚያድግበት ራስ ከሆነው ጋራ ግንኙነት የለውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እንዲህ ያለ ሰው ራስ ከሆነው ከክርስቶስ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፤ አካልን በሙሉ በመገጣጠሚያና በጅማት አያይዞ የሚመግበው ራስ ነው። እግዚአብሔር ለአካል ሙሉ ዕድገት የሚሰጠውም በዚህ ዐይነት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ሥጋ ሁሉ ጸንቶ በሚ​ኖ​ር​በት፥ በሥ​ርና በጅ​ማ​ትም በሚ​ስ​ማ​ማ​በት፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሚ​ያ​ድ​ግ​በ​ትና በሚ​ጸ​ና​በት፥ በሚ​ሞ​ላ​በ​ትም በራስ አይ​ጸ​ናም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እንደዚህ ያለ ሰው ራስ ወደሚሆነው አይጠጋም፥ ከእርሱም አካል ሁሉ በጅማትና በማሰሪያ ምግብን እየተቀበለ እየተጋጠመም፥ እግዚአብሔር በሚሰጠው ማደግ ያድጋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ቈላስይስ 2:19
33 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም ለዘለዓለምም ክብር ይሁን! አሜን።


በመጨረሻም ሁላችሁ በአንድ ልብ ሁኑ፤ እርስ በእርሳችሁ ተሳሰቡ፤ በወንድማማችነት ፍቅር ተዋደዱ፤ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ።


እንዲህም የምጋደለው ልባቸው እንዲጽናና፥ በፍቅርም በአንድነት እንዲተሳሰሩ፥ በፍጹም ማስተዋልም የሚገኘውን ባለጠግነት ሁሉ እንዲኖራቸው፥ የእግዚአብሔርንም ምሥጢር እርሱንም ክርስቶስን እንዲያውቁ ነው፤


በእርግጥ በመላ መቄዶንያ ላሉት ወንድሞች ሁሉ እንዲሁ አድርጋችኋል። ነገር ግን ወንድሞች ሆይ! እነዚህን አብዝታችሁ እንድታደርጉ


ጌታ እንድትበዙ ያድርጋችሁ፤ እኛም ለእናንተ ፍቅርን እንዳበዛንላችሁ እንዲሁም የእርስ በርሳችሁንና ለሁሉ ሰው ያላችሁን ፍቅር ያብዛ።


ወንድሞች ሆይ! እምነታችሁ እጅግ አድጎአልና፥ የእናንተም የእያንዳንዳችሁ ሁሉ ፍቅር ለእርስ በርሳችሁ በዝቶአልና፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ልናመሰግን ግዴታ አለብን፤


እርሱም አካሉ የሆነችው የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው፤ እርሱ በሁሉ ነገር ቀዳሚ በመሆን መጀመሪያ ነው፤ ከሙታንም በኩር ነው።


በዚህም በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁና በእግዚአብሔር እውቀት እያደጋችሁ፥ ለጌታ እንደሚገባው ፍጹም ደስ የሚያሰኘውን ሕይወት እንድትኖሩ ነው።


ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ብቻ ኑሩ፤ በዚህም መጥቼ ባያችሁ ወይም ብርቅ፥ በአንድ ልብ ስለ ወንጌል እምነት አብራችሁ መጋደላችሁንና በአንድ መንፈስ ጸንታችሁ መቆማችሁን እሰማለሁ።


ማንም የራሱን እካል የሚጠላ ከቶ የለምና፤ ይመግበዋል፤ ይንከባከበውማል። ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን ያደረገው እንዲህ ነው፤


በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ።


ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት፤ ከሁሉ በላይም ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው።


እኔ ተከልሁ፤ አጵሎስም አጠጣ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ያሳድግ ነበር፤


ነገር ግን ወንድሞች ሆይ! ሁላችሁ ተስማምታችሁ በአንድ ልቡና እና በአንድ አቋም በአንድነት የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ።


ነገር ግን ከቅርንጫፎቹ አንዳንዱ ቢሰበሩ አንተም የበረሃ ወይራ የሆንህ በመካከላቸው ገብተህ ከእነርሱ ጋር የወይራ ዘይት ከሚወጣው ሥር ተካፋይ ከሆንህ፥


ያመኑትም ሕዝብ አንድ ልብ አንዲትም ነፍስ ነበሩአቸው፤ ገንዘባቸውም ሁሉ በአንድነት ነበረ እንጂ ካለው አንድ ነገር ስንኳ የራሱ እንደሆነ ማንም አልተናገረም።


ይህም ሁሉም አንድ እንዲሆኑ፥ አንተም፥ አባት ሆይ! በእኔ እንዳለህና እኔም በአንተ እንዳለሁ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ እንዲሆኑ፥ አንተም እንደ ላክኸኝ ዓለም እንዲያምን ነው።


ነገር ግን የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፥ የሴትም ራስ ወንድ፥ የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር መሆኑን እንድታውቁ እወዳለሁ።


እርሷም አካሉና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ ናት።


በእርሱ ሕንጻ ሁሉ አንድ ላይ ተገጣጥሞ በጌታ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንዲሆን ያድጋል።


አዲሱን የወይን ጠጅ ግን በአዲስ አቁማዳ ማኖር ይገባል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች