Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




አሞጽ 9:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 “እነሆ፥ አራሹ አጫጁን፥ ወይን ጠማቂውም ዘሪውን የሚቀድምበት ወራት ይመጣል፥” ይላል ጌታ፤ “ተራሮችም ጣፋጭ የወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ፥ ኮረብቶችም ሁሉ ይቀልጣሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ዐጫጁ ዐጭዶ ሳይጨርስ፣ ዐራሹ በላዩ የሚደርስበት፣ ችግኝ ተካዩም ገና ተክሎ ሳይጨርስ፣ ወይን ጨማቂው የሚደርስበት ጊዜ ይመጣል፤ አዲስ የወይን ጠጅ ከተራሮች ይንጠባጠባል፤ ከኰረብቶችም ሁሉ ይፈስሳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእህል ሰብል አጫጆች አጭደው ሳይጨርሱ፥ አራሾች የሚደርሱባቸውና ወይን ጨማቂዎችም የወይን ፍሬ ጨምቀው ሳይጨርሱ፥ የወይን ተካዮች የሚደርሱባቸው ጊዜ ይመጣል፤ በዚያን ጊዜ ተራራዎች ጣፋጭ የወይን ጠጅ ያፈልቃሉ፤ ኰረብቶችም በወይን ጠጅ ይጥለቀለቃሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 “እነሆ፥ እን​ዲህ ያለ ወራት ይመ​ጣ​ልን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እርሻ ከአ​ጨዳ ጋር፥ ዘርም ከእ​ሸት ጋር አንድ ይሆ​ናል፤ ከተ​ራ​ሮ​ችም ማር ይፈ​ስ​ሳል፤ ኮረ​ብ​ታ​ውም ይለ​መ​ል​ማል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እነሆ፥ አራሹ አጫጁን፥ ወይን ጠማቂውም ዘሪውን የሚያገኝበት ወራት ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ተራሮችም በተሀውን የወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ፥ ኮረብቶችም ሁሉ ይቀልጣሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




አሞጽ 9:13
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ውርንጫውን በወይን ግንድ ያስራል፥ የአህያይቱንም ግልገል በወይን አረግ፥ ልብሱን በወይን ያጥባል፥ መጎናጸፊያውንም በወይን ደም።


ተራሮችም በጌታ ፊት፥ ከምድር ሁሉ ጌታ ፊት እንደ ሰም ቀለጡ።


ደስታና ሐሴትም ከፍሬያማው እርሻ ተወስዶአል፤ በወይኑም ቦታዎች ዝማሬና እልልታ የለም፤ በመጥመቂያም ወይን የሚረግጥ የለም፤ የረጋጮቹን እልልታ አጥፍቻለሁ።


በእሾህም ፈንታ ጥድ፥ በኩርንችትም ፈንታ ባርሰነት ይበቅላል፤ ለጌታም መታሰቢያና ለዘለዓለምም የማይጠፋ ምልክት ይሆናል።


ተዘልለውም ይቀመጡባታል፤ ቤቶችንም ይሠራሉ ወይኑንም ይተክላሉ በዙሪያቸውም ባሉ በሚንቋቸው ሁሉ ላይ ፍርድን ባደረግሁ ጊዜ ተዘልለው ይቀመጣሉ፤ እኔም ጌታ አምላካቸው እንደሆንሁ ያውቃሉ።


“ባድማ የነበረች ይህች ምድር እንደ ዔድን ገነት ሆነች፤ የወደሙት፥ ባድማ የሆኑት፥ የፈረሱት ከተሞች አጥር ተሰርቶላቸዋል፥ መኖሪያም ሆነዋል” ይላሉ።


አውድማዎችም እህልን ይሞላሉ፥ መጥመቂያዎችም የወይን ጠጅንና ዘይትን አትረፍርፈው ያፈስሳሉ።


በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፥ ተራሮች አዲስ ወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ፥ ኮረብቶችም ወተትን ያፈስሳሉ፥ በይሁዳም ያሉት ፈፋዎች ሁሉ ውኃን ያጐርፋሉ፥ ከጌታም ቤት ምንጭ ትፈልቃለች፥ የሰጢምንም ሸለቆ ታጠጣለች።


ነገር ግን ይሁዳ ለዘለዓለም፥ ኢየሩሳሌምም ለልጅ ልጅ መኖሪያ ይሆናል።


ለእናተም እህሉን ማበራየቱ የወይኑን ዘለላ እስከሚቆረጥበት ወቅት ድረስ ይደርሳል፥ የወይኑንም ዘለላ መቁረጥ እህል እስከ ሚዘራበት ወቅት ድረስ ይደርሳል፤ እስክትጠግቡም ድረስ እንጀራችሁን ትበላላችሁ፥ በምድራችሁም ላይ በደኅንነት ትቀመጣላችሁ።


ጌታ የሠራዊት አምላክ ምድርን ይዳስሳል እርሷም ትቀልጣለች፥ የሚኖሩባትም ሁሉ ያለቅሳሉ፤ ሞላዋም እንደ ግብጽ ወንዝ ትነሣለች፥ ዳግመኛም እንደ ግብጽ ወንዝ ትወርዳለች።


እናንተ ‘ገና አራት ወር ቀርቶአል፤ ከዚያም መከር ይመጣል፤’ ትሉ የለምን? እነሆ እላችኋለሁ፤ ዐይናችሁን አንሡ፤ እርሻው ከወዲሁ ለአዝመራ እንዴት እንደ ደረሰ ተመልከቱ።


ከእስራኤል አምላክ ከጌታ ፊት፥ በሲናው ጌታ ፊት ተራሮች ቀለጡ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች