አሞጽ 6:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 የሞተውን ሰው የሚያቃጥለው ዘመዱ አጥንቱን ከቤቱ አንስቶት ባወጣው ጊዜ፥ በቤቱም በውስጠኛው ክፍል ያለውን፦ “በእዚያ እስከ አሁን ድረስ ከአንተ ጋር ሰው አለን?” ይለዋል፥ እርሱም፦ “ማንም የለም” ይላል፤ ያንጊዜ፦ “የጌታን ስም ልንጠራ አይገባንምና ዝም በል” ይለዋል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 በድኖቹንም ከቤት አውጥቶ ማቃጠል ያለበት አንድ ዘመድ መጥቶ ተደብቆ ያለውን ሰው፣ “ከአንተ ጋራ የቀረ ሌላ ሰው አለን?” ሲለው፣ እርሱም “የለም” ይለዋል፤ ከዚያም በኋላ፣ “ዝም በል፤ የእግዚአብሔርን ስም መጥራት አይገባንም” ይለዋል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ከሟቾቹ የአንዱ የቅርብ ዘመድ የሆነና ሥርዓተ ቀብሩን የሚፈጽም ሬሳውን ከቤት አውጥቶ ይወስዳል፤ በዚያን ጊዜ በቤት ውስጥ ያለውን አንድ ሰው ጠርቶ “ከአንተ ጋር የቀረ ሌላ ሰው አለን?” ብሎ ይጠይቀዋል፤ ሰውየውም “ማንም የቀረ የለም!” ብሎ ይመልስለታል፤ ጠያቂውም “የእግዚአብሔርን ስም መጥራት ስለማይገባን ዝም በል!” ይለዋል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 አጥንቶቻቸውንም ከቤት ያወጡ ዘንድ ቤተሰቦቻቸው በወሰዱአቸው ጊዜ፥ ቤት ጠባቂውን በአንተ ዘንድ የቀረ አለን? በአለው ጊዜ እርሱ የለም ይላል። ያም የእግዚአብሔርንም ስም እንዳትጠራ ዝም በል ይለዋል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 አጥንቱንም ከቤቱ ያወጡ ዘንድ የሰው ዘመድና አቃጣዩ ባነሡት ጊዜ፥ በቤቱም ውስጥ ያለውን፦ እስከ አሁን ድረስ ገና ሰው በአንተ ዘንድ አለን? ባለው ጊዜ፥ እርሱም፦ ማንም የለም ባለ ጊዜ፥ ያን ጊዜ፦ የእግዚአብሔርን ስም እንጠራ ዘንድ አይገባንምና ዝም በል ይለዋል። ምዕራፉን ተመልከት |
ከዚህም በኋላ ኢዮስያስ ዙሪያውን ሲመለከት፥ በኰረብቶች ላይ የተሠሩ መቃብሮችን አየ፤ በእነዚያም መቃብሮች ውስጥ የነበረውን ዐፅም ሁሉ አስወጥቶ በመሠዊያው ላይ በእሳት አቃጠለው፤ በዚህም ዓይነት መሠዊያው የረከሰ መሆኑን አስገነዘበ፤ ኢዮስያስ ይህንን ሁሉ በማድረጉ ከብዙ ጊዜ በፊት በተደረገ የአምልኮ በዓል ላይ ንጉሥ ኢዮርብዓም በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ ሳለ ነቢዩ የተናገረው የትንቢት ቃል ተፈጸመ፤ ንጉሥ ኢዮስያስ ዙሪያውን ሲመለከት ይህን ትንቢት ተናግሮ የነበረው ነቢይ የተቀበረበትን መካነ መቃብር አይቶ፥