Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




አሞጽ 5:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላልና፦ “ሺህ ከሚወጣበት ከተማ መቶ ይቀርላታል፥ መቶም ከሚወጣባት ከተማ ለእስራኤል ቤት ዐሥር ይቀርላታል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “አንድ ሺሕ ብርቱዎችን ለእስራኤል የምታዘምት ከተማ፣ አንድ መቶ ብቻ ይቀሯታል፤ አንድ መቶ ብርቱዎችን የምታዘምተውም፣ ዐሥር ብቻ ይቀሯታል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከአንዲት የእስራኤል ከተማ ሺህ ጦረኞች ይዘምታሉ፤ በሕይወት የሚቀሩት ግን አንድ መቶ ብቻ ይሆናሉ፤ ከሌላይቱም ከተማ መቶ ጦረኞች ይዘምታሉ፤ ተመልሰው የሚመጡት ግን ዐሥር ብቻ ይሆናሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “ሺህ ከሚ​ወ​ጡ​ባት ከተማ መቶ ይቀ​ራሉ፤ መቶም ከሚ​ወ​ጡ​ባት ከተማ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ዐሥር ይቀ​ራሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላልና፦ ሺህ ከሚወጣበት ከተማ መቶ ይቀርላታል፥ መቶም ከሚወጣባት ከተማ ለእስራኤል ቤት አሥር ይቀርላታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




አሞጽ 5:3
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ላሞቻቸንም የሰቡ ይሁኑ፥ ቅጥራቸውም መፍረሻና መውጫ አይኑረው፥ በአደባባዮቻችንም ዋይታ አይኑር፥


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፤ እንደ ሰዶም በሆንን ገሞራንም በመሰልን ነበር።


እስራኤል ሆይ፤ ሕዝብህ እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆንም፤ የተረፉት ብቻ ይመለሳሉ። ታላቅና ጻድቅ የሆነ ጥፋት ታውጆአል።


ከዐሥር አንድ ሰው እንኳን በምድሪቱ ቢቀር፤ እርሱም ደግሞ ይጠፋል፤ ነገር ግን የኮምበልና የባሉጥ ዛፍ በተቈረጠ ጊዜ ጉቶ እንደሚቀር፤ ቅዱሱም ዘር እንዲሁ በምድሪቱ ጉቶ ሆኖ ይቀራል።”


በሚሄዱባቸው አሕዛብ መካከል ርኩሰታቸውን ሁሉ እንዲናገሩ ከእነርሱ ጥቂቶች ከሰይፍ፥ ከራብና ከቸነፈር አስቀራለሁ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


እንዲህም ይሆናል፤ ዐሥር ሰዎች በአንድ ቤት ውስጥ ቢቀሩ እነርሱ ይሞታሉ።


ኢሳይያስም ስለ እስራኤል እንዲህ ሲል ይጮኻል፦ “የእስራኤል ልጆች ቍጥር እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆንም ትሩፋን ይድናሉ፤


ለጌታ ለእግዚአብሔር ስላልታዘዛችሁ እንደ ሰማይ ከዋክብት በዝታችሁ የነበራችሁት እናንተ ጥቂት ብቻ ትቀራላችሁ።


ጌታ እናንተን በማበልጸግና ቁጥራችሁን በማብዛት ደስ ይለው እንደ ነበረ፥ እንዲሁ ጌታ እናንተን ሲያጠፋችሁና ሲያፈራርሳችሁም ደስ ይለዋል፤ እንድትወርሱአት ከምትገቡባት ምድር ትነቀላላችሁ።


ጌታም በአሕዛብ መካከል ይበትናችኋል፥ ጌታ በውስጣቸው በሚያኖራችሁ በአሕዛብ መካከልም ጥቂቶች ሆናችሁ ትቀራላችሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች