Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




አሞጽ 5:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የእስራኤል ቤት ሆይ! እኔ በእናንተ ላይ ለሙሾ የማነሣውን ይህን ቃል ስሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ስለ እናንተ የምደረድረውን ይህን የሙሾ ቃል ስሙ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በእናንተ ላይ እኔ የማወርደውን ይህን ሙሾ አድምጡ፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! በእ​ና​ንተ ላይ ለሙሾ የማ​ነ​ሣ​ውን ይህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በእናንተ ላይ ለሙሾ የማነሣውን ይህን ቃል ስሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




አሞጽ 5:1
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ በአሕዛብ መካከል፦ እንዲህ ያለ ነገር ማን ሰምቶአል? ብላችሁ ጠይቁ። የእስራኤል ድንግል በጣም የሚያስደነግጠውን ነገር አድርጋለች።


ጌታ የቁጣውን ትውልድ ጥሎአልና፥ ትቶታልምና ጠጉርሽን ቁረጪ፥ ጣዪውም፥ በተራቈቱ ኮረብቶችም ላይ ሙሾን አውጪ፥” ትላቸዋለህ።


“ለተራሮች ልቅሶንና እንጉርጉሮን ለምድረ በዳ ማሰማርያዎችም ዋይታን አነሣለሁ፥ ሰው እንዳያልፍባቸው ባድማ ሆነዋልና። ሰዎችም የከብቱን ድምፅ አይሰሙም፤ ከሰማይ ወፎች ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ሸሽተው ሄደዋል።


የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “አስተውሉ፥ እንዲመጡም አልቃሾች ሴቶችን ጥሩ፤ እንዲመጡም ወደ ብልሃተኞች ሴቶች ላኩ፤


እናንተ ሴቶች ሆይ! የጌታን ቃል ስሙ፥ ጆሮአችሁም የአፉን ቃል ትቀበል፥ ለሴቶች ልጆቻችሁም ልቅሶውን፥ እያንዳንዳችሁም ለባልንጀሮቻችሁ ዋይታውን አስተምሩ።


በውኑ ስለ እነዚህ ነገሮች አልቀስፋቸውምን? ይላል ጌታ፤ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?


አንተም በእስራኤል ልዑሎች ላይ ሙሾ አሙሽ፥


ከቅርንጫፍዋ እሳት ወጣች፥ ፍሬዋንም በላች፥ ለገዢዎች በትረ መንግሥት የሚሆን ብርቱ ቅርንጫፍ በእርሷ ዘንድ የለም። ይህ ሙሾ ነው፥ ለልቅሶም ይሆናል።


በአንቺ ላይ ሙሾ ያወርዳሉ፥ እንዲህም ይሉሻል፦ ከባሕር የተቀመጥሽ በባሕርም ውስጥ የጸናሽ፥ ከሚቀመጡብሽም ጋር በዙሪያሽ የሚኖሩትን ሁሉ ያስፈራሽ፥ ዝነኛ ከተማ ሆይ፥ እንዴት ጠፋሽ!


አንተ የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ጢሮስ ሙሾ አውርድ፥


የሰው ልጅ ሆይ፥ በጢሮስ ንጉሥ ላይ ሙሾ አሞሽተህ እንዲህ በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጥበብን የተሞላህ ውበትህም የተፈጸመ መደምደሚያ አንተ ነህ።


የሚያወርዱት ሙሾ ይህ ነው፤ የአሕዛብ ቆነጃጅት፤ በግብጽና ብዛትዋ ሁሉ ላይ ሙሾን ያወርዳሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ግብጽ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ሙሾ አውርድ፥ እንዲህም በለው፦ በሕዝቦች መካከል አንበሳ መሰልህ፥ እንደ ባሕር አውሬ ነበርህ፤ በወንዞችህም ገንፍለህ ወጥተሃል፥ ውኃውንም በእግርህ አደፍርሰሃል፥ ወንዞችህንም አሳድፈሃል።


የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታ በእናንተ ላይ፥ ከግብጽ ምድር ባወጣሁት ወገን ሁሉ ላይ የተናገረውን ይህን ቃል ስሙ፤


“እናንተ በሰማርያ ተራራ ያላችሁ፥ ድሆችንም የምትበድሉ፥ ችግረኛውንም የምትጨቁኑ፥ ጌቶቻቸውንም፦ ‘አምጡ እንጠጣ’ የምትሉ እናንተ የባሳን ላሞች ሆይ! ይህን ቃል ስሙ።


ስለዚህ ጌታ፥ የሠራዊት አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ “በየአደባባዩ ሁሉ ላይ ዋይታ ይሆናል፤ በየመንገዱም ሁሉ ላይ ‘ወዮ! ወዮ!’ ይላሉ፤ ገበሬዎቹም ወደ ልቅሶ፥ አልቃሾቹም ወደ ዋይታ ይጠራሉ።


አሺማ በምትባል የሰማርያ ጣኦት የሚምሉና፦ ‘ዳን ሆይ! ሕያው አምላክህን!’ ደግሞ፦ ‘ሕያው የቤርሳቤህን መንገድ!’ ብለው የሚምሉ፥ እነርሱ ይወድቃሉ፥ ዳግመኛም አይነሡም።”


በዚያ ቀን ምሳሌ ይመስልባችኋል፥ በኀዘን እንጉርጉሮ ያለቅስላችኋል፤ እርሱም፦ “ፈጽመን ጠፍተናል፤ የሕዝቤን ድርሻ ቀየረ፤ ከእኔ እንዴት ወሰደው፤ እርሻችንን ለከዳተኞች ይከፋፍላል” ይላል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች