አሞጽ 1:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ገለዓድን የብረት ጥርስ ባለው መውቅያ አበራይተውታልና ስለ ሦስት የደማስቆ ኃጢአት ስለ አራትም መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የደማስቆ ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም፤ የብረት ጥርስ ባለው ማሄጃ፣ ገለዓድን አሂዳለችና፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የደማስቆ ሕዝብ ደጋግመው ስለ ሠሩት ኃጢአት ያለ ጥርጥር እቀጣቸዋለሁ፤ እነርሱ የገለዓድን ሕዝብ የብረት ጥርስ ባለው መንኰራኲር አበራይተው አሠቃይተዋቸዋል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የገለዓድን ነፍሰ ጡሮች በብረት መጋዝ ሰንጥቀዋቸዋልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የደማስቆ ኀጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስላቸውም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ገለዓድን በብረት መንኰራኵር አሂዶአልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የደማስቆ ኃጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም። ምዕራፉን ተመልከት |