Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሐዋርያት ሥራ 9:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ሳውልም ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከደቀ መዛሙርት ጋር ይተባበር ዘንድ ሞከረ፤ ሁሉም ደቀመዝሙር እንደሆነ ስላላመኑ ፈሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ሳውልም ወደ ኢየሩሳሌም በመጣ ጊዜ፣ ከደቀ መዛሙርት ጋራ ለመቀላቀል ሞከረ፤ እነርሱ ግን በርግጥ ደቀ መዝሙር መሆኑን ስላላመኑ ሁሉም ፈሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ሳውል ወደ ኢየሩሳሌም በሄደ ጊዜ እዚያ ካሉት ደቀ መዛሙርት ጋር ለመደባለቅ ሞከረ፤ እነርሱ ግን የእርሱ በክርስቶስ ማመን እውነት ስላልመሰላቸው ሁሉም ፈሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ሳው​ልም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በደ​ረሰ ጊዜ ሊገ​ና​ኛ​ቸው ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትን ፈለ​ጋ​ቸው። ሁሉም ፈሩት፤ የጌ​ታ​ችን ደቀ መዝ​ሙር እንደ ሆነ አላ​መ​ኑ​ትም ነበ​ርና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ሳውልም ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከደቀ መዛሙርት ጋር ይተባበር ዘንድ ሞከረ፤ ሁሉም ደቀ መዝሙር እንደ ሆነ ስላላመኑ ፈሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐዋርያት ሥራ 9:26
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚያን ጊዜ ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ፤ እርስ በርሳቸውም ይጠላላሉ፤


ነገር ግን አስቀድሜ በደማስቆ ላሉት በኢየሩሳሌምም በይሁዳም አገር ሁሉ ለአሕዛብም ንስሓ ይገቡ ዘንድና ለንስሓ የሚገባ ነገር እያደረጉ ወደ እግዚአብሔር ይመለሱ ዘንድ ተናገርሁ።


ተፈትተውም ወደ ወገኖቻቸው መጡና የካህናት አለቆችና ሽማግሌዎች ያሉአቸውን ሁሉ ነገሩአቸው።


ደቀ መዛሙርት ግን በሌሊት ወስደው በቅጥር ላይ አሳልፈው በቅርጫት አወረዱት።


ይህም ወደ ባርነት ሊመልሱን በክርስቶስ ኢየሱስ ያለንን ነጻነታችንን ሊሰልሉ ሾልከው በስውር ስለ ገቡ ስለ ሐሰተኞች ወንድሞች ነበረ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች