Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሐዋርያት ሥራ 8:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ያነበውም የነበረ የመጽሐፉ ክፍል ይህ ነበረ፤ “እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፤ የበግ ጠቦትም በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ጃንደረባው ያነብብ የነበረው የመጽሐፍ ክፍል ይህ ነበር፤ “እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፤ በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ፣ አፉን አልከፈተም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 እርሱም ያነበው የነበረው የቅዱስ መጽሐፍ ክፍል የሚከተለው ነበረ፦ “እርሱ ለመታረድ እንደሚነዳ በግ ነበረ፤ ሲሸልቱትም ዝም እንደሚል ጠቦት፤ እርሱም ለመናገር አፉን አልከፈተም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ያነ​በው የነ​በረ የመ​ጽ​ሐፉ ቃልም እን​ዲህ የሚል ነበር፤ “እንደ በግ ወደ መታ​ረድ ተነዳ፤ የበግ ጠቦ​ትም በሚ​ሸ​ል​ተው ፊት እን​ደ​ማ​ይ​ና​ገር እን​ዲሁ አፉን አል​ከ​ፈ​ተም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ያነበውም የነበረ የመጽሐፉ ክፍል ይህ ነበረ፤ እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፥ የበግ ጠቦትም በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐዋርያት ሥራ 8:32
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንደ ጠቦቶችና እንደ አውራ በጎች እንደ አውራ ፍየሎችም ወደ መታረድ አወርዳቸዋለሁ።


ይህም “ስለ አንተ ቀኑን ሙሉ እንገደላለን፤ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን፤” ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።


እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ እንደ የዋህ በግ ጠቦት ሆንሁ፤ እነርሱም፦ “ዛፉን ከነፍሬው እናጥፋ፥ ስሙም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታወስ ከሕያዋን ምድር እናስወግደው” ብለው ምክርን እንዳሰቡብኝ አላወቅሁም ነበር።


ከመተላለፌ ሁሉ አድነኝ፥ የሞኞች መሳለቂያ አታድርገኝ።


በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፥ ክፉ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ ሁሉ በአፌ ላይ ልጓም አኖራለሁ አልሁ።


በማግሥቱ ኢየሱስ ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ “እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።


አቤቱ! አንተ ግን፥ አውቀኸኛል፤ አይተኸኛል፥ ልቤንም ወደ አንተ መሆኑን ፈትነሃል፤ እንደ ሚታረድ በግ ጐትተህ ለያቸው፥ ለመታረድም ቀን አዘጋጃቸው።


ነገር ግን ነውርና እድፍ እንደሌለው በግ ደም፥ በክርስቶስ ክቡር ደም ነው፥


ኢየሱስም “አባት ሆይ! የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው፤” አለ። ልብሱንም ዕጣ ተጣጥለው ተካፈሉት።


ለሚቃጠል መሥዋዕት አንድ ወይፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአንድ ዓመት ተባት ጠቦት፤


እርሱም “የሚመራኝ ሳይኖር ይህ እንዴት ይቻለኛል?” አለው። ወጥቶም ከእርሱ ጋር ይቀመጥ ዘንድ ፊልጶስን ለመነው።


እኔ የተቀበልሁትንና ከሁሉ በላይ የሆነውን ለእናንተ አስተላልፌአለሁ፤ ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚሉት ክርስቶስ ለኀጢአታችን ሞተ፤


ለሚቃጠልም መሥዋዕት አንድ ወይፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአንድ ዓመት ተባት ጠቦት፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች