Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሐዋርያት ሥራ 7:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 በማግሥቱም እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አገኛቸው፤ ሊያስታርቃቸውም ወዶ ‘ሰዎች ሆይ! እናንተስ ወንድማማች ናችሁ፤ ስለምን እርስ በርሳችሁ ትበዳደላላችሁ?’ አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 በማግስቱም ደግሞ ሁለት እስራኤላውያን ሲጣሉ ደረሰ፤ ሊያስታርቃቸውም ፈልጎ፣ ‘ሰዎች፤ እናንተ እኮ ወንድማማቾች ናችሁ፤ እንዴት እርስ በርሳችሁ ትጐዳዳላችሁ?’ አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 በማግስቱም ሁለት እስራኤላውያን እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አገኘና ሊገላግላቸው በመፈለግ ‘እናንተ ሰዎች፥ እናንተ ወንድማማች ናችሁ፤ ስለምን ትጣላላችሁ?’ አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 በማ​ግ​ሥ​ቱም ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ሁለት ሰዎች እርስ በር​ሳ​ቸው ሲጣሉ አገኘ፤ ሊያ​ስ​ታ​ር​ቃ​ቸ​ውም ወድዶ፦ ‘እና​ን​ተማ ወን​ድ​ማ​ማ​ቾች ናችሁ፤ እርስ በር​ሳ​ችሁ ለምን ትጣ​ላ​ላ​ችሁ?’ አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በማግሥቱም እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አገኛቸው፥ ሊያስታርቃቸውም ወዶ፦ ‘ሰዎች ሆይ፥ እናንተስ ወንድማማች ናችሁ፤ ስለ ምን እርስ በርሳችሁ ትበዳደላላችሁ?’ አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐዋርያት ሥራ 7:26
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አብራምም ሎጥን አለው፦ እኛ ወንድማማች ነንና በእኔና በአንተ በእረኞቼና በእረኞችህ መካከል ጠብ እንዳይሆን እለምንሃለሁ።


ከዚያም ዮሴፍ ወንድሞቹን አሰናበታቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ “በመንገድ እርስ በርሳችሁ አትጣሉ።”


የዳዊት የዕርገት መዝሙር። ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ እንዴት መልካም፥ እንዴት ውብ ነው።


የተበደለ ወንድም እንደ ጸናች ከተማ ጽኑ ነው፥ ክርክራቸውም እንደ ግንብ ብረት ነው።


ወዲያውም ሕዝቡን እስኪያሰናብት ድረስ ደቀመዛሙርቱ ወደ ጀልባ ገብተው ወደ ማዶ እንዲቀድሙት ግድ አላቸው።


ወንድሞቹም እግዚአብሔር በእጁ መዳንን እንዲሰጣቸው የሚያስተውሉ ይመስለው ነበር፤ እነርሱ ግን አላስተዋሉም።


ስለዚህ ለእናንተ በክርስቶስ አንዳች መበረታተታት ቢሆን፥ የፍቅር መጽናናትም ቢሆን፥ የመንፈስም ኅብረት ቢሆን፥ ምሕረትና ርኅራኄም ቢሆኑ፥


ከራስ ወዳድነት ወይም ከትምክሕት የተነሣ አንድም ነገር አታድርጉ፤ ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው በትሕትና ባልንጀራውን ከራሱ ይልቅ እንደሚሻል አድርጎ ይቁጠር፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች