Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሐዋርያት ሥራ 28:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እነርሱም “እኛ ከይሁዳ ስለ አንተ ደብዳቤ አልተቀበልንም፤ ከወንድሞችም አንድ ስንኳ መጥቶ ስለ አንተ ክፉ ነገር አላወራልንም፤ ወይም አልተናገረብህም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እነርሱም እንዲህ አሉት፤ “ስለ አንተ ከይሁዳ ምድር የተጻፈ አንድም ደብዳቤ አልደረሰንም፤ ከዚያ የመጡ ወንድሞችም ስለ አንተ ያቀረቡት ወይም የተናገሩት አንዳች መጥፎ ነገር የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፦ “ከይሁዳ ምድር ስለ አንተ ጉዳይ የተጻፈ ደብዳቤ አልደረሰንም፤ ወደዚህ ከመጡ ሰዎች ማንም ስለ አንተ ክፉ ያወራ ወይም የተናገረ የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የአ​ይ​ሁድ ታላ​ላቅ ሰዎ​ችም እን​ዲህ አሉት፥ “ለእ​ኛስ ከይ​ሁዳ ሀገር ስለ አንተ መል​እ​ክት አል​ደ​ረ​ሰ​ንም፤ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከመ​ጡት ወን​ድ​ሞ​ችም ቢሆን አንድ ስንኳ ከዚህ አስ​ቀ​ድሞ ስለ አንተ ክፉ ነገር ያወ​ራን፥ የነ​ገ​ረ​ንም የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እነርሱም፦ “እኛ ከይሁዳ ስለ አንተ ደብዳቤ አልተቀበልንም፥ ከወንድሞችም አንድ ስንኳ መጥቶ ስለ አንተ ክፉ ነገር አላወራልንም ወይም አልተናገረብህም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐዋርያት ሥራ 28:21
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም፤ በፍርድም የሚነሣብሽን ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የጌታ አገልጋዮች ርስት ይህ ነው፥ ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው፥ ይላል ጌታ።


የሚያጸድቀኝ ቅርብ ነው፤ ከእኔስ ጋር የሚከራከር ማን ነው? በአንድነት እንቁም፤ የሚከራከረኝ ማን ነው? ወደ እኔ ይቅረብ።


እነሆ፥ የሚቆጡህ ሁሉ ያፍራሉ፥ ይዋረዳሉም፤ የሚከራከሩህም እንዳልነበሩ ይሆናሉ፥ ይጠፋሉም።


እንዲህም ሊቀ ካህናቱ ደግሞ ሽማግሌዎቹም ሁሉ ይመሰክሩልኛል፤ ከእነርሱ ደግሞ መልእክትን ለወንድሞቻቸው ተቀብዬ፥ በደማስቆ ያሉትን ደግሞ ታስረው እንዲቀጡ ወደ ኢየሩሳሌም ላመጣ ወደዚያ እሄድ ነበር።


በእስራኤል ልጆች መካከል ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ውሻ ምላሱን አያንቀሳቅስባቸውም ይህም ጌታ በግብጽና በእስራኤል መካከል እንደለየ እንድታውቁ ነው።


“አሁንም፥ ወንድሞቼ ሆይ! እናንተ እንደ አለቆቻችሁ ደግሞ ባለማወቅ እንዳደረጋችሁት አውቄአለሁ፤


በዚያም ወንድሞችን አግኝተን በእነርሱ ዘንድ ሰባት ቀን እንድንቀመጥ ለመኑን፤ እንዲሁም ወደ ሮሜ መጣን።


ስለ ሥጋ ዘመዶቼና ስለ ወንድሞቼ ስል እኔ ራሴ ከክርስቶስ ተለይቼ የተረገምሁ እንድሆን እመኝ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች