ሐዋርያት ሥራ 27:41 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)41 ነገር ግን ሁለት ባሕር በተገናኙበት ስፍራ ወድቀው መርከቡን በዲብ ላይ ነዱ፤ በስተ ፊቱም ተተክሎ የማይነቃነቅ ሆነ፤ በስተ ኋላው ግን ከማዕበሉ ግፊያ የተነሣ ይሰበር ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም41 ነገር ግን መርከቡ ከአሸዋ ቍልል ጋራ ተላትሞ መሬት ነካ፤ የፊተኛው ክፍሉም አሸዋው ውስጥ ተቀርቅሮ አልነቃነቅ አለ፤ የኋለኛው ክፍሉም በማዕበሉ ክፉኛ ስለ ተመታ ይሰባበር ጀመር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም41 ነገር ግን መርከቡ ከአሸዋ ቊልል ጋር በመጋጨቱ ቊልቊል ተደፋ፤ በስተፊቱም ወደ ታች ተተክሎ የማይነቃነቅ ሆነ፤ በስተኋላው ግን ከማዕበሉ ግፊት የተነሣ ይሰባበር ጀመር። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)41 መርከቢቱም በሁለት ታላላቅ ድንጋዮች መካከል ተቀረቀረች፤ ባሕሩም ጥልቅ ነበረ። ከወደፊቷም ተያዘች፤ አልተንቀሳቀሰችምም፤ ከሞገዱም የተነሣ በስተኋላ በኩል ጎንዋን ተሰብራ ተጐረደች፤ ቀዛፊዎችም ወደፊት ሊገፉአት አልቻሉም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)41 ነገር ግን ሁለት ባሕር በተገናኙበት ስፍራ ወድቀው መርከቡን በዲብ ላይ ነዱ፤ በስተ ፊቱም ተተክሎ የማይነቃነቅ ሆነ፥ በስተ ኋላው ግን ከማዕበሉ ግፊያ የተነሣ ይሰበር ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |