ሐዋርያት ሥራ 27:40 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)40 መልሕቆቹንም ፈትተው በባሕር ተዉአቸው፤ ያን ጊዜም የመቅዘፊያውን ማሠሪያ ፈቱት፤ ታናሹንም ሸራ ለነፋስ ከፍ አድርገው ወደ ዳር አቅንተው ይሄዱ ዘንድ ጀመሩ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም40 ከዚያም መልሕቆቹን ቈርጠው ባሕር ውስጥ ጥለው ሄዱ፤ የመቅዘፊያውንም ገመድ በዚያው ጊዜ ፈቱ፤ የፊተኛውንም ሸራ ለነፋስ ከፍ አድርገው ወደ ባሕሩ ዳርቻ አቀኑ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም40 መልሕቆቹን ፈተው በባሕር ውስጥ ለቀቁአቸው፤ በዚያኑ ጊዜም የመቅዘፊያውን ገመዶች ፈቱ፤ ከዚህ በኩል ያለውን ሸራ ወደ ነፋሱ ከፍ አድርገው ወደ ባሕሩ ዳርቻ ለመውጣት ሄዱ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)40 መልሕቁንም ፈትተው በባሕር ላይ ጣሉት፤ የሚያቆሙበትንም አመቻችተው እንደ ነፋሱ አነፋፈስ መጠን ትንሹን ሸራ ሰቀሉ፤ ወደ ባሕሩ ዳርቻም ሄድን። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)40 መልሕቆቹንም ፈትተው በባሕር ተዉአቸው፥ ያን ጊዜም የመቅዘፊያውን ማሠሪያ ፈቱት፤ ታናሹንም ሸራ ለነፋስ ከፍ አድርገው ወደ ዳር አቅንተው ይሄዱ ዘንድ ጀመሩ። ምዕራፉን ተመልከት |