Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሐዋርያት ሥራ 27:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 በዐሥራ አራተኛውም ሌሊት በአድርያ ባሕር ወዲህና ወዲያ ስንነዳ፥ መርከበኞች በእኩለ ሌሊት ወደ አንድ ምድር የቀረቡ መሰላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 በዐሥራ አራተኛው ሌሊት በአድርያ ባሕር ላይ ከወዲያ ወዲህ ስንገላታ፣ እኩለ ሌሊት ገደማ መርከበኞቹ ወደ መሬት የተቃረቡ መሰላቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 በዐሥራ አራተኛው ሌሊት በአድርያ ባሕር መካከል ላይ በነፋስ እየተንገላታን ስንሄድ እኩለ ሌሊት ላይ መርከበኞች ወደ ምድር የቀረቡ መሰላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛ​ውም ቀን በመ​ን​ፈቀ ሌሊት በአ​ድ​ርያ ባሕር ስን​ጓዝ ቀዛ​ፊ​ዎች ወደ የብሱ የደ​ረሱ መሰ​ላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 በአሥራ አራተኛውም ሌሊት በአድርያ ባሕር ወዲህና ወዲያ ስንነዳ፥ መርከበኞች በእኩለ ሌሊት ወደ አንድ ምድር የቀረቡ መሰላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐዋርያት ሥራ 27:27
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይህን የሚያህል ታላቅ ሀብት በአንድ ሰዓት ጠፍቶአልና፤” የመርከብም መሪ ሁሉ በመርከብም ወደ ማናቸውም ስፍራ የሚሄድ ሁሉ መርከበኞችም ከባሕርም የሚጠቀሙ ሁሉ በሩቅ ቆሙ፤


መርከበኞቹም ከመርከቡ ይሸሹ ዘንድ ፈልገው ከመርከቡ በስተ ፊት መልሕቅ መጣል እንዳላቸው አመካኝተው ታንኳይቱን ወደ ባሕር ባወረዱ ጊዜ፥


የመርከቡ አለቃ ወደ እርሱ ቀርቦ፦ “እንዴት ትተኛለህ? ተነሥ አምላክህን ጥራ፥ ምናልባትም እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ያስበን ይሆናል” አለው።


ንጉሥ ኪራምም ከሰሎሞን ሰዎች ጋር የሚያገለግሉ የሠለጠኑ መርከበኞችን ላከለት።


ነገር ግን ወደ አንዲት ደሴት እንድንወድቅ ያስፈልገናል።


መለኪያ ገመድም ቢጥሉ ሃያ በሰው ቁመት አገኙ ጥቂትም ቆይተው ሁለተኛ ቢጥሉ ዐሥራ አምስት በሰው ቁመት አገኙ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች