ሐዋርያት ሥራ 27:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 በእስያም ዳርቻ ወዳሉ ስፍራዎች ይሄድ ዘንድ ባለው በአድራሚጢስ መርከብ ገብተን ተነሣን፤ የመቄዶንያም ሰው የሆነ የተሰሎንቄው አርስጥሮኮስ ከእኛ ጋር ነበረ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 ከአድራሚጢስ ተነሥቶ በእስያ አውራጃ ባሕር ዳርቻ ላይ ወዳሉት ወደቦች በሚሄደው መርከብ ተሳፍረን የባሕር ጕዞ ጀመርን፤ በተሰሎንቄ ይኖር የነበረው የመቄዶንያ ሰው፣ አርስጥሮኮስም ከእኛ ጋራ ነበረ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 በእስያ የባሕር ዳርቻ ወዳሉት ወደቦች በሚሄደው የአድራሚጥዮን መርከብ ተሳፍረን ተጓዝን፤ በተሰሎንቄ የሚኖረው የመቄዶንያው ሰው አርስጥሮኮስም ከእኛ ጋር ነበረ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 በተነሣንም ጊዜ ወደ እስያ በምትሄድ በአድራማጢስ መርከብ ተሳፈርን፤ የተሰሎንቄ ሀገር ሰው የሚሆን መቄዶንያዊው አርስጥሮኮስም አብሮን ሄደ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 በእስያም ዳርቻ ወዳሉ ስፍራዎች ይሄድ ዘንድ ባለው በአድራሚጢስ መርከብ ገብተን ተነሣን፤ የመቄዶንያም ሰው የሆነ የተሰሎንቄው አርስጥሮኮስ ከእኛ ጋር ነበረ። ምዕራፉን ተመልከት |