Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሐዋርያት ሥራ 26:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 አሁንም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለአባቶቻችን ስለ ተሰጠው ስለ ተስፋ ቃል አለኝታ ልፋረድ ቆሜአለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 አሁንም ተከስሼ እዚህ የቀረብሁበት ምክንያት፣ እግዚአብሔር ለአባቶቻችን ቃል የገባውን ነገር ተስፋ በማድረጌ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 አሁን ግን ለፍርድ እዚህ የቆምኩት እግዚአብሔር ለአባቶቻችን ስለ ሰጠው የቃል ኪዳን ተስፋ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 አሁ​ንም ከጥ​ንት ጀምሮ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን የተ​ሰ​ጠ​ውን ተስፋ በመ​ታ​መን ከፍ​ርድ በታች ቆሜ​አ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 አሁንም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለአባቶቻችን ስለ ተሰጠው ስለ ተስፋ ቃል አለኝታ ልፋረድ ቆሜአለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐዋርያት ሥራ 26:6
59 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነዚህም ራሳቸው ደግሞ የሚጠብቁት፥ ጻድቃንም ዐመፀኞችም ከሙታን ይነሡ ዘንድ እንዳላቸው ተስፋ በእግዚአብሔር ዘንድ አለኝ።


እንዲሁም የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እንድንጠብቅ ያስተምረናል፤


ስለዚህም ምክንያት አያችሁና እነግራችሁ ዘንድ ጠራኋችሁ፤ ስለ እስራኤል ተስፋ ይህን ሰንሰለት ለብሻለሁና።”


ለአባቶች የተሰጠውን የተስፋ ቃል ሊያጸና፤ ስለ እግዚአብሔር እውነት ክርስቶስ ለተገረዙት አገልጋይ ሆነ እላለሁ፤


ጳውሎስ ግን እኩሌቶቹ ሰዱቃውያን እኩሌቶቹም ፈሪሳውያን መሆናቸውን አይቶ “ወንድሞች ሆይ! እኔ ፈሪሳዊ የፈሪሳዊም ልጅ ነኝ፤ ስለ ተስፋና ስለ ሙታን መነሣት ይፈርዱብኛል፤” ብሎ በሸንጎው ጮኸ።


ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፤ በጎቹም እንዲበተኑ እረኛውን ምታ፤ እጄንም በታናናሾች ላይ አዞራለሁ።


ስለዚህ ወላጂቱ እስከምትወልድበት ጊዜ ድረስ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፤ ከዚህ በኋላ የቀሩት ወንድሞቹ ወደ እስራኤል ልጆች ይመለሳሉ።


“አምላክህ ጌታ ከገዛ ወንድሞችህ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣልሃል፤ እርሱን አድምጥ።


ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ፥ እነዚህንም ምድሮች ሁሉ ለዘርህ እሰጣለሁ፥ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ፥


ቃሌን ሰምተሃልና፥ የምድር አሕዛብ ሁሉም በዘርህ ይባረካሉ።”


የሚባርኩህንም እባርካለሁ፥ የሚረግሙህንም እረግማለሁ፥ የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ።


የዘመኑ ሙላት በመጣ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግ ሥር የተወለደውን ልጁን ላከ፤


እግዚአብሔር ሙታንን የሚያስነሣ እንደሆነ ስለምን በእናንተ ዘንድ የማይታመን ነገር ሆኖ ይቆጠራል?


ሁለተኛም ከሳሙኤል ጀምሮ ከእርሱም በኋላ የተናገሩት ነቢያት ሁሉ ደግሞ ስለዚህ ወራት ተናገሩ።


ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ ግን የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፤ እናንተም ትወጣላችሁ፥ ከጋጣ እንደ ወጡ ጥጃዎች ትቦርቃላችሁ።


እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፤ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፤ የምትደሰቱበትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


በዚያ ቀን ለዳዊት ቤትና ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ከኃጢአትና ከርኩሰት የሚያነጻ ምንጭ ይፈልቃል።


አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ! አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ! እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።


የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ስሙ ቁጥቋጥ የሚባል ሰው በስፍራው ይበቅላል፥ የጌታንም መቅደስ ይሠራል።


ከቀድሞ ዘመን ጀምረህ ለአባቶቻችን እንደማልህላቸው እውነትን ለያዕቆብ፥ ርኅራኄን ለአብርሃም ታደርጋለህ።


በዔሳውም ተራራ ላይ ይፈርዱ ዘንድ አዳኞች ወደ ጽዮን ተራራ ላይ ይወጣሉ፥ መንግሥቱም ለጌታ ይሆናል።


እንዲህም ይሆናል፥ የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፥ ጌታም እንደ ተናገረ፥ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም የሚተርፉ ይኖራሉ። ደግሞም ጌታ የጠራቸው ይገኛሉ።


ከዚያም በኋላ የእስራኤል ልጆች ተመልሰው አምላካቸውን ጌታንና ንጉሣቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ፤ በኋለኛውም ዘመን ፈርተው ወደ ጌታና ወደ መልካምነቱ ይመጣሉ።


አገልጋዬ ዳዊት ንጉሥ ይሆናቸዋል፤ ሁሉም አንድ እረኛ ይኖራቸዋል፤ በፍርዴ ይሄዳሉ፥ ትእዛዜን ይጠብቃሉ ይፈጽሟቸዋልም።


ባድማ፥ ባድማ፥ ባድማ አደርጋታለሁ፤ ፍርድ ያለው እስኪመጣ ድረስ ይህች ደግሞ አትሆንም፥ ለእርሱም እሰጣለሁ።


ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፤ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።


በዚያን ቀን የጌታ ዛፍ ቅርንጫፍ ውብና የከበረ ይሆናል፤ የምድሪቱም ፍሬ ከጥፋት ለተረፈው የእስራኤል ወገን


በዚያ ለዳዊት ቀንድን አበቅላለሁ፥ ለቀባሁትም ሰው መብራትን አዘጋጃለሁ።


ጌታ ለዳዊት በእውነት ማለ አይጸጸትምም፥ እንዲህ ብሎ፦ ከሆድህ ፍሬ በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ።


ጌታ ማዳኑን አስታወቀ፥ በአሕዛብም ፊት ጽድቁን ገለጠ።


በትረ መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፥ የገዥም ዘንግ ከእግሮቹ መካከል፥ ገዥ የሆነው እስኪመጣ ድረስ፥ የአሕዛብ መታዘዝም ለእርሱ ይሆናል።


“በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ “በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፥ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትነድፋለህ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች