ሐዋርያት ሥራ 26:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)32 አግሪጳም ፈስጦስን “ይህ ሰው እኮ ወደ ቄሣር ይግባኝ ባይል ይፈታ ዘንድ ይቻል ነበር፤” አለው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም32 አግሪጳም ፊስጦስን፣ “ይህ ሰው ወደ ቄሳር ይግባኝ ባይል ኖሮ መልቀቅ ይቻል ነበር” አለው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም32 አግሪጳም ፊስጦስን “ይህ ሰው ወደ ሮሙ ንጉሠ ነገሥት ይግባኝ ባይል ኖሮ በነጻ በተለቀቀ ነበር” አለ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)32 አግሪጳም ፊስጦስን፥ “ወደ ቄሣር ይግባኝ ባይል ኖሮ ይህ ሰው ይፈታ ዘንድ በተገባ ነበር” አለው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)32 አግሪጳም ፈስጦስን፦ ይህ ሰው እኮ ወደ ቄሣር ይግባኝ ባይል ይፈታ ዘንድ ይቻል ነበር” አለው። ምዕራፉን ተመልከት |