Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሐዋርያት ሥራ 24:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ሁለት ዓመትም ከሞላ በኋላ ጶርቅዮስ ፊስጦስ በፊልክስ ፈንታ ተተካ። ፊልክስም አይሁድን ደስ ያሰኝ ዘንድ ወዶ ጳውሎስን እንደታሰረ ተወው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላም፣ ፊልክስ በጶርቅዮስ ፊስጦስ ተተካ፤ ፊልክስም አይሁድን ለማስደሰት ሲል፣ ጳውሎስን እንደ ታሰረ ተወው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ከሁለት ዓመት በኋላ ጶርቅዮስ ፊስጦስ በፊልክስ ቦታ ተተካ፤ ፊልክስ አይሁድን ደስ ለማሰኘት ፈልጎ ጳውሎስን እንደ ታሰረ ተወው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ሁለት ዓመ​ትም ካለፈ በኋላ፥ ፊል​ክስ ተሻ​ረና ጶር​ቅ​ዮስ ፊስ​ጦስ የሚ​ባል ሌላ ሀገረ ገዢ በእ​ርሱ ቦታ መጣ፤ ፊል​ክ​ስም በግ​ልጥ ለአ​ይ​ሁድ ሊያ​ዳላ ወደደ፤ ስለ​ዚ​ህም ጳው​ሎ​ስን እንደ ታሰረ ተወው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ሁለት ዓመትም ከሞላ በኋላ ጶርቅዮስ ፊስጦስ በፊልክስ ፈንታ ተተካ። ፊልክስም አይሁድን ደስ ያሰኝ ዘንድ ወዶ ጳውሎስን እንደ ታሰረ ተወው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐዋርያት ሥራ 24:27
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ፊስጦስ ግን አይሁድን ደስ ያሰኝ ዘንድ ወዶ ጳውሎስን “ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተህ ስለዚህ ነገር ከዚያው በፊቴ ትፋረድ ዘንድ ትወዳለህን?” ብሎ መለሰለት።


በዚያውም ብዙ ቀን ስለ ተቀመጡ ፊስጦስ የጳውሎስን ነገር ለንጉሡ እንዲህ ብሎ ገለጠ “ፊልክስ አስሮ የተወው አንድ ሰው በዚህ አለ፤


አይሁድንም ደስ እንዳሰኛቸው አይቶ ጨምሮ ጴጥሮስን ደግሞ ያዘው። የቂጣ በዓልም ወራት ነበረ።


ፊስጦስም ወደ አውራጃው ገብቶ ከሦስት ቀን በኋላ ከቂሣርያ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።


ጲላጦስም ሕዝቡን ደስ ለማሰኘት ሲል በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን ገርፎ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠው።


አሁን ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሳምናለሁን? ወይስ ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? እስከ አሁን ሰውን ደስ የማሰኝ ብሆን ኖሮ የክርስቶስ ባርያ አልሆንም ነበር።


አግሪጳም ፈስጦስን “ይህ ሰው እኮ ወደ ቄሣር ይግባኝ ባይል ይፈታ ዘንድ ይቻል ነበር፤” አለው።


ሰውን መፍራት ወጥመድ ያመጣል፥ በጌታ የሚታመን ግን እርሱ ይጠበቃል።


ጳውሎስም በተከራየው ቤት ሁለት ዓመት ሙሉ ተቀመጠ፤ ወደ እርሱም የሚመጡትን ሁሉ ይቀበል ነበር፤


ፊስጦስ ግን ጳውሎስ በቂሳርያ እንዲጠበቅ እርሱም ራሱ ወደዚያ ፈጥኖ ይሄድ ዘንድ እንዳለው መለሰላቸው፤


“ከሳሾችህ ደግሞ ሲመጡ እሰማሃለሁ፤” አለው፤ በሄሮድስም ግቢ ውስጥ ይጠብቁት ዘንድ አዘዘ።


ክፉ ለማድረግ ብዙ ሰዎችን አትከተል፤ ፍርድንም ለማጣመም ከብዙ ሰዎች ጋር ተስማምተህ አትመስክር።


ኤርምያስንም በገመዱ ጐተቱት፤ ከጉድጓድም አወጡት፤ ኤርምያስም በእስር ቤት አደባባይ ተቀመጠ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች